የክትባት አገልግሎት ለማሻሻል የማህበረሰቡ ድርሻ የጎላ ነዉ ተባለ።ቢሮዉ
የአፍሪካ ክትባት ሳምንት አከባበሪን አስመልክቶ በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ መንደር 50 ነዋሪዎች ጋር መክሯል።
የክትባት አገልግሎት ለማሻሻል የማህበረሰቡ ድርሻ የጎላ ነዉ ተባለ።ቢሮዉ
የአፍሪካ ክትባት ሳምንት አከባበሪን አስመልክቶ በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ መንደር 50 ነዋሪዎች ጋር መክሯል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የጤና ትምህርት ባለሙያዎች አቶ መርቅኔ ዑመር በዉይይቱ ወቅት እንደአሉት የክትባት አገልግሎት ለማሻሻል የህብረተሰቡ ድርሻ የጎላ መሆኑን ነው ።
አብዛኛዉ በህፃናት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎችን በክትባት መከላከል ሲንችል ህፃናትን በወቅቱ ካለማስከተብ የሚከሰቱ መሆናቸውን የገለፁት አቶ መርቅኔ ህፃናት በወቅቱ እንዲከተቡ ለማድረግ የወላጆች ሚና የጎላ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት የዉይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል ።
በዉይይቱ ላይ ስለክትባት ጠቄሜታ፣ህፃናትን ለማስከተብ የወላጆች ግዴታ እና ከክትባት ጋር ተያይዞ በሚተላለፉ ቁልፍ መልዕክቶች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል ።
በዉይይት መድረኩ ላይ ከባምባሲ ወረዳው የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣መንደር 50 ቀበሌ አመራሮች፣እናቶች፣የሃይማኖት አባቶች፣የጤና ኤክቴሸን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።