በሪፎርሙ ቴክኒካል ቡድን ታይቶ የተከለሰ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ስልጣን እና ተግባራት (ረቂቅ)
- ጤናን የሚመለከቱ ፣ ሕጎችን ያመነጫል፣ስትራቴጂዎችን ይነድፋል፣ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- የጤናውን ዘርፍ ልማት ክልላዊ ፕሮግራም ይነድፋል፣እቅድ ያወጣል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲዳረስ ድጋፍ ያደርጋል፤የጤና መሠረተ ልማት እንዲስፋፋ፤ በሰው ኃይል፤ በህክምና መሣሪያ እና በሌሎች ግብዓት የተሟላ እንዲሆን ድጋፍ ያደርጋል፤
- የአካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያን፣ ስደተኞች እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገ የጤና አገልግሎት እንዲደራጅ ድጋፍ ያደርጋል፤ይከታተላል፤
- የጤና ምርምር የአሰራር ስርዓት ይዘርጋል፤ የምርምር ማዕከላትን ያቋቁማል፤ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ክልላዊ የሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፤
- ወረርሽኝና ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመተንበይ የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀይሳል፣ የፈጣን ምላሽ እና የመልሶ ማገገም ተግባራትን ያስተባብራል፤ ይከታተላል፤
- የኅብረተሰቡን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ሁኔታዎችን የመከላከል እርምጃ ይወስዳል፣ ድንገተኛ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ሌሎች አካላትን በማስተባበር ለችግሩ አፋጣኝና ውጤታማ እንደ አስፈላጊነቱ አስገዳጅ መፍትሄ ይሰጣል፤
- አግባብነት ያላቸውን የተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም የጤና አጠባበቅ ትምህርት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- የመድኃኒቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች እና የህክምና ግብዓቶች በቂ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል፤ የአገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ ድጋፍ ያደርጋል፤ይደግፋል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- የሆስፒታሎችን አስተዳደር በበላይነት ይመራል፤ይደግፋል፤የዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታሎችን አቅም በማጎልበት ረገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ይሠራል፤ የጤና አገልግሎቱን በበላይነት ይቆጣጠራል፣ይደግፋል፤
- የጤናውን ዘርፍ የሰው ሀብት ልማት እና አስተዳደር ስትራቴጂ ይነድፋል፤ተግባራዊ ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይሰራል፤
- የምግብ እና የመድኃኒት ምርቶች ጥራት፤ ፈዋሽነት፤ እና ደህንነት ቁጥጥር ሥራዎች በአግባቡ መፈጸማቸውን ይከታተላል፤
- የሀገር በቀል እውቀት እና ተደጋጋፊ ወይም አማራጭ ህክምና አገልግሎት ከዘመናዊው ህክምና ጋር እንዲቀናጅና ከዘመናዊው መድኃኒት ጎን ለጎን እንዲሰራ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይሰራል፤
- ክልላዊ የጤና መድህን ሥርዓት ይዘርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይመራል፤
- ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ለማዳረስ የጤና ፋይናንሲንግ ስትራቴጂ ይነድፋል፣ ሀብት ያስባስባል፣ ያስተባብራል፤ይመራል፤
- የጤና ባለሙያዎችን እና የጤናና ጤና ነክ ተቋማትን በተመለከተ የቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ሀገራዊ ደረጃዎችንና መስፈርቶችን እንዲወጣላቸዉ ከሚመለከታቸዉ ጋር ይሰራል፤ ተፈጻሚነታቸዉን ይቆጣጠራል፤
- በጤና አገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋይ ደህንነትና መብት የሚከበርበትን አሰራር ይዘረጋል ፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የደም፣ ህዋስ፣ ህብረ ህዋስ፣ የአካል ክፍልና የአካል ልገሳ እና ንቅለ ተከላ አገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤
- የቴሌ ጤና፣ የኑክሌር ህክምና እና ሌሎች አዳዲስ የጤና አገልግሎቶችን ለማሳደግ እና ለማስፋፋት የሚረዱ የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ አስገዳጅ ደረጃዎችን ያወጣል፣ አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
- የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ስርዓቶችን ለማጠናከር ማስረጃዎች እና እውቀቶችን ያመነጫል፣ የመረጃ ትንተና እና ችግር ፈቺ ጥናቶችን ያደርጋል፤ አዳዲስ እና የአሠራር ስርዓቶችን ይነድፋል፤ የሙከራ እና የማስፋፊያ ትግበራ ስራዎችን ያስተባብራል፣ የቴክኒክ እና የትግበራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤ የአመራር እና የሰው ሃይል አቅምን በማሳደግ እና በኢትዮጵያ እንዲሁም በአለም አቀፍ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ትብብር መድረክ እና የልህቀት ማዕከል ሆኖ እንዲቋቋም ያደርጋል።
- የቅድመ ጤና ተቋም የህክምና አገልግሎት እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ ቋት ያደራጃል፤ በሃገሪቱ የሚገኝ የጤና መረጃ ይሰበሰባል፤ የመረጃ ደህንነት፣ ግላዊነት እና የመረጃ ልውውጥን የሚያረጋግጥ ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስተዳድራል ፤ተደራሽ ያደርጋል፤
- ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ በአጋርነት የሚሰሩበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤
- የሜዲካል ቱሪዝም በአገሪቷ እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፤ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በትብብር ይሰራል፤
- በክልሉ የአካል ድጋፍና ተሃድሶ አገልግሎት መዘርጋቱን ያረጋግጣል፤ ይደግፋል፤
- የአካባቢ፣የእንሰሳትና የሰው ጤና በቅንጅት የሚሰሩበትን የአሰራር ስርዓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይዘረጋል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- የዘርፈ ብዙ ምላሽ ለሚፈልጉ የጤና ችግሮች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አሰራርና ዓቅም እንዲገነባ ይደረጋል፡፡
- የጤና መማከርት ጉባዔ ማቋቋሚያ ህግ ያረቃል፣ ሲጸድቅ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ ያደረጋል፤ ይከታተላል፤
