በሀገር አቀፍ የተጀመረዉን የስቭል ሰርቨስ ሪፎርም በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጤና ቢሮ ሀላፊ ገለጹ፡፡ ቢሮ ለሪፎርሙ ስራ አጋጅ የሆኑ ሰነዶችን የመገምግምና የማጽደቅ ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከሰኔ 19/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለጤና ዘርፍ አገልግሎት እና አስተዳደር ሪሮርም ትግበራ የሚረዱ የተዘጋጁ ሰነዶችን የመገምገም፤ የመተቸት እና ከማኔጅመንቱ ግብዓትን በማሰባሰብን እና የማጽደቅ ስራዎችን ሲሰሩ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
ይህ ስራ ዛሬም ተጠናክሮ በመቀጠል የጤና ዘርፍ የክፍያ እና ፋይናንስ ሪፎርም እቅድ፤
የነፃ እና ገልልተኛ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ እስትራቴጅ፤የብዝሃነት እና አካታችነት ረቂቅ ማኑዋል ሰነድ፤የሪፎርሙ የኮሚኒኬሽን እስትራቴጂ ዕቅድ፤የሪፎርሙ ወረቀት አልባ ስርዓት እቅድ ገምግሞ የማጽደቅ ስራዎች ተከናዉኗል፡፡
ለሪፎርሙ መሳካት አስፈላጊ ተብለዉ እንደሀገር የተቀመጡ ሰነዶች እና እስትራተጂካዊ ዕቅዶች የመገምግምና የማጽደቅ ስራዎች እሰክጠናቀቅ ድረስ ሰነዶችን የመገምግምና የማጽደቅ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ የቢሮ ሀላፊዉ ገልጸዉ ያልተጠናቀቁ ስራዎች በሪፎርሙ ቴክኒካል ኮሚቴዎች በኩል በየጊዜዉ ተጠናቀዉ ለማኔጅመንት መቅረብ እንዳላባቸዉ አሳስበዋል፡፡
