የክሊኒካል አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

በክሊኒካል አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስር የሚሰሩ ዋና ዋና ተግባራት

  • የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣
    • የተከለሰውን የጤና ጣቢያዎች ሪፎርም አፈጻጸም መከታተያ ዳሽቦርድ ከመጀመሪያው ስልጠና በኋላ በተደረጉ ለውጦች ላይ በየደረጃ ላሉ ባለሙያዎች ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ
    • ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ክፍሎች መፍጠር፤
    • የቤተሰብ ጤና ቡድን (FHT) ማጠናከር እና በቂ የኪት (KIT) አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ፤
    • የኦአር ብሎክ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ጤና ጣቢያዎችን በግብዓትና በሰው ሃይል በማሟላት አገልግሎት ማስጀመርና ማጠናከር፣
    • ጽዱ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃዶችን መፍጠር መከታተልና ድጋፍ ማድረግ
    • የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አጠባበቅ ጥምረት ለጥራት (EPAQ) ማጠናከር
    • የኢትዮጵያ ጤና ጣቢያ ማሻሻያ ትግበራ መመሪያን (EHCRIG) እንዲተገበር ማድርግ
    • የጥራት ማሻሻያ (QI) ፕሮጀክቶችን እና ክሊኒካዊ የግንኙነት ችሎታዎችን በPHCU ደረጃ መንደፍ እና መተግበር
    • የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ክሊኒካል መመሪያ /EPHCG/ አተገባበርን ማጠናከር
    • በቂ፣ ዕቃቸው የተሟላ መሰረታዊ እና የተሻሻለ አምቡላንስ አቅርቦትን እንዲሟላ ማድረግ፤
    • በጤና ተቋም ላይ የተመሰረተ የድንገተኛ እና የህጻናትን የፅኑ ህክምና አገልግሎት እንዲጠናከር ትኩረት ሰጥቶ መስራትና ማጠናከር
    • ወሳኝ የምርመራ፣ የናሙና ቅብብሎሽ እና የመጠባበቂያ (backup) አገልግሎት ተደራሽነት ማሻሻል፤
    • ክሊኒካል ኦዲት፣ የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ለጥራት (HSTQ) እና የሜንተርሺፕ ፕሮግራም ማጠናከር፤
    • 5ተኛው ዙር የሆስፒታል ጥምረት ለጥራት ማረጋገጫ (CROWN) ትግበራን ማጠናከር።
    • የቀዶ ሕክምና የሕይወት አድን (SaLT) ትግበራ መድገፍና ማጠናከር
    • ስፔሻሊቲ እና ሰብ–ስፔሻሊቲ አገልግሎቶችን ተደራሽነትን ማረጋገጥ፤
    • የሜዲካል ኦክሲጅን ምርት እና አቅርቦትን ደረጃ እና ጥራት ማሳደግ፤
    • ጥራት ያለው ስፔሻሊቲ የጤና አገልግሎቶችን (የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች፣ የአይን እና የቆዳ ቀዶ ህክምና አገልግሎቶች) ተደራሽነት ማሻሻል፤
    • የአጣጠር ችግር (የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ (cleft palate and lip) አገልግሎት ማጠናከር፤
    • በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ደም አቅርቦት በጤና ተቋማት እንዲሻሻል መደገፍ
    • ደረጃዎችን ያሟላ ላቦራቶሪዎች እንዲኖሩ አጠናክሮ መስራት ፤
    • ክልላዊ የላቦራቶሪ ግንኙነት እና የናሙና ቅብብሎሽ ስርዓትን ማጠናከር
    • የውጭ እና የውስጥ ተገልጋዬች እርካታ ደሰሳ ማካሄድ፡
    • የለውጥ መሳሪያዎች እና የዜጐች ቻርተር ተግባራዊ እንዲሆን መከታተል መደገፍ
    • በሆስፒታሎች የመልካም አስተዳደር ኢንዴክስ ተግባራዊ ማድረግ፤
    • የካይዘን የአመራር ፍልስፍና ተግባራዊነት ማጠናከር
    • የሞት ኦዲት ለጥራት ማሻሻያ ስርዓትን በመማሪያ ማዕከላት እና SBFR ሆስፒታሎች ማስጀመር እና ትግበራውን መከታተል
    • የመጀመሪው ምዕራፍ የሥርዓት ማነቆች ላይ ያተኮረ የሙከራ ሪፎርም (SBFR) ትግበራ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን ማስፋት (Scaling up)
    • የተቀናጀ የመድሃኒት ሎጂስቲክ (IPLS)፤ የትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓቱን እንዲጠናከር ማድረግ፤
    • በጤና ተቃማት የኤለክትሮኒክ የጤና ግብዓት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓት (DAGU) ትግበራ ማስፋፋትና ማጠናከር
    • ጠንካራ የአስቸኳይ ጊዜ የመድሃኒት አቅርቦት አስተዳደር (Emergency supply chain management) ስርዓት ማዳበር እና ተግባራዊ ማድረግ፤
    • በጤና ተቋማት የመድኃኒትና ህክምና መማክርት (DTC) አፈፃፀሙን (functionality) መከታተልና ማሻሻል
    • ወጥ የሆነ የመድኃኒት መረጃ ስርዓት መዘርጋት፤
    • የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ የመድኃኒት አቅርቦት በጤና ተቋማት እንዲኖር ማድረግ (Quantification)
    • የህክምና መሳሪያዎች መረጃ ስርዓትን (MEMIS) ማስፋፋትና ማጠናከር
    • የሕክምና መሣሪያዎች ተከላ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አያያዝ መኖሩን ማረጋገጥ
    • የባህል ህክምና በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ሚና ማጠናክር
    • የግሉ ዘርፍ በጤናዉ ሴክተር ያለዉን አስተዋጽኦ ማጠናከር፤
    1. በዳይሬክቶሬቱ የወጡ ደንቦች፤መመሪያዎችና አዎጆች
    • የጤና ግበዓቶችን ለመቀያየር እና አዘዋውሮ ለመጠቀም የወጣ የአሰራር መመሪያ ቁጥር 04/2016
    • በቤ/ጉ/ክ/መንግስት የህክምና ኦክስጅን ምርት አስተዳደርን፤ ስርጭትን እና አጠቀቀምን ለመወሰን የወጣ የመስተዳድር መመሪያ ቁጥር 071/2017
    • የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክና አፈፃፃም መመሪያ ቁጥር 6/2006
    1. ከዳይሬክቶሬቱ ጋር የሚስሩ ባለድርሻ አካላት፤
    • የቢሮው ሁሉም ዳይሮክቶሬቶች
    • ከተጠሪ ጤና ተቋማት (ደም ባንክ፤የአካል ጎዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል፤ የቤ/ጉ/ክ/መንግስት/የህ/ጤ/ም/ላ/ ተቋም፤ የፓዌ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
    • የመድኃኒት አቅቦት አገልግለት አሶሳ ቅርንጫፍ፤
    • የመድኃኒት አቅቦት አገልግለት ባህርዳር ቅርንጫፍ፤
    • የጤና ተቋማት
    • የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
    • የቤ/ጉ/ክ/መ/መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ
    • የቤ/ጉ/ክ/መ/ ፍትህ ቢሮ