በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የአመራር ለዉጥ ተደረገ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገለፀ። ቢሮዉ ከአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የማናጅመንት አባላት ጋር መክሯል ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በዉይይቱ ወቅት እንደአሉት ቢሮዉ በሆስፒታሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ከሆስፒታሉ ማናጀመንት ጀምሮ ከሆስፒታሉ ከፍተኛ ሀኪሞች ጋር በተደጋጋሚ ዉይይት የተደረገ ቢሆንም በሆስፒታሉ የሚሰጠዉ አገልግሎት የደንበኞችን እርካታ መጨመር አለመቻሉን ነዉ።
ይህንን ተደጋጋሚ ችግሮች በመቅረፍ በሆስፒታሉ የህብረተሰቡን እርካታ መጨመር የሚችሉ አገልግሎት ለመስጠት የሆስፒታሉ የቦርድ አባላት እና የሆስፒታሉ ማናጅመንት አባላት የአመራር ለዉጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የማናጅመንት አባላት ለዉጥ መደረጉን አቶ ወልተጂ ተናግረዋል ። በዚሁ መሰረት፡-
1. የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የቦርድ ሰብሳቢ፣
2. የጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ፣
3. የአሶሳ ከተማ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አባል
4. የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አባል እንዲሁም የነበሩ የህዝብ እና የሰራተኛ ተወካዮች በነበሩበት እንዲቀጥሉ ተደርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ
1.አቶ አወድ ሱሌማን የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስከያጅ፣
2.ዶ/ር መብራቱ ገ/መድን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር
3.ዶ/ር አብዮት ደርሶ የጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ ተሰይመዋል ።
ይህ የአመራር ለዉጥ የተደረገዉ በሆስፒታሉ የተሳለጠ አገልግሎት በመስጠት ሥራና ሰራተኛን ለማገናኘት የተደረገ ሽግሽግ በመሆኑ በአዲስ የተተኩት የሆስፒታል ማናጅመንት አባላት ሥራቸውን በትጋትና ለዉጥ ማምጣት በሚችል መልኩ በመምራት የማህበረሰቡን እርካታ መጨመር እንዳለባቸዉ አቶ ወልተጂ ተናግረዋል ።
የቢሮዉ ኃላፊ አክለውም ሆስፒታሉ የሚሰጠዉን አገልግሎት እና የሆስፒታሉን የዉስጥ ገቢ ማሻሻል ወሳኝ በመሆኑ ሆስፒታሉ የራሱን ገቢ የሚያመነጭበት ስልቶን መንደፍ እንዳለበት ገልፀው የፋይናንስ አስተዳደር እና የፋርማሲ አገልግሎት ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ገልጸዋል ።
የሆስፒታሉን አገልግሎት ለማሻሻል የሆስፒታሉ ማናጅመንት ለሚያደርጋቸው ማንኛውም እንቅስቃሴዎች በቢሮ በኩል አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግ የቢሮ ሀላፊው አስገንዝበዋል ።
መጋቢት 29/2018 ዓ.ም


Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.