ቀበሌዎችን ሞደል ማድረግ የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም ለማሳለጥ የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተገለፀ ።

ቀበሌዎችን ሞደል ማድረግ የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም ለማሳለጥ የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተገለፀ ።

በኡንዱሉ ወረዳ የቤርሚሊ ቀበሌ የሞዴልነት መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ ።

አንድ ቀበሌ ሞዴል ሆኖ ለመመረጥ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን አሟልቶ በመገኘት ፍትሀዊና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ፣የመረጃ አብዮት የመረጃ ጥራትና አያያዝ እንዲሁም የጤና ኬላ ሪፎርም አተገባበርን መሠረት ያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት በአሶሳ ዞን ኡንዱሉ ወረዳ ቤርሚሊ ቀበሌ የሞዴልነት መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ ተመርቋል ።

በምርቃት ስነስርአቱ ለይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የኡንዱሉ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብዱልባጂ መሀመድ በዛሬው እለት በሞዴልነት ለመመረቅ የበቃው በርሚሊ ቀበሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና የቀበሌ አመራሮች ጠንካራ ተሳትፎ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ኃላፊው አገላለፅ ይህ ውጤት የተመዘገበው በአመራሩ ድጋፍና በማህበረሰብ ጠንካራ ተሳትፎ በመሆኑ ማህበረሰቡ የሚሰራውን ነገር ተረድቶና አምኖ በመቀበሉ ውጤት ማምጣት መቻሉን በመግለፅ በቀጣይ የተሻለ ሰርተን በወረዳች የሚገኙ ሁሉንም ቀበሌዎች ሞዴል ማድረግ እንደምንችል ያየንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

ቀቤለውን ሞዴል ለማድረግ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና የቀበሌ አስተዳዳሪ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው ለተገኘው አጥጋቢ ውጤት በቀበሌው መስተዳደርና በማህበረሰቡ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የኡንዱሉ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እስማኤል ሙክታር በበኩላቸው የአመራሩ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና የማህበረሰቡ ቅንጅታዊ አሰራር ቀበሌውን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ሞደል ማድረግ እንደሚቻል በርሚሊ ቀበሌ አንዱ ማሳያ በመሆኑ ሌሎች ቀበሌዎችም ከዚህ መማር አለባቸዉ ብለዋል።

ቀሪ ቀበሌዎችን ሙሉ በሙሉ ሞደል ለማድረግ በወረዳ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት ተቋማትና የግል ባለሀብቶች ከጤና ጽ/ቤት ጋር በጋራና በመተጋገዝ መስራት እንደአለባቸዉ ጠይቀዋል ።

ኃላፊዉ አክለዉም ሞዴል ቀበሌ ማስመረቅ ብቻውን ግብ ሳይሆን ሞዴል የሆኑ ቀበሌዎችን ሞዴልነታቸውን አስጠብቀውና አሻሽለው ማስቀጠል ሲቻል እንደሆነ በመግለጽ ለዚህም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።

በእለቱ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪን ጨምሮ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ፣የኡንዱሉ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ:የወረዳው አፈ ጉባኤ እና ሌሎች አካላት በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙ ሲሆን በዕለቱ አስር ብር ለአንድ እናት በሚል የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ገብ የተካሄደ ሲሆን ለሞደል ቤተሰብ ምረቃ የተሻለ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *