በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ከልላዊ  መንግስት  ጤና ቢሮ በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ  ተግባራት ከባለፈው  አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑን ቢሮው  ገለፀ። በ2018 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተደርጓል ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ከልላዊ  መንግስት  ጤና ቢሮ በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ  ተግባራት ከባለፈው  አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑን ቢሮው  ገለፀ። በ2018 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተደርጓል ።

በበጀት አመቱ በጤናው ዘርፍ በፕሮግራም  እና በአስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት  የሥራ አፈጻጸም በቢሮ የጤና መሠረተ ልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ሪፎርም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዑሱማን አብዱላሂ  ቀርቦ ዉይይት  ተደርጎበታል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት  ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በሥራ አፈጻጸም መድረክ ማጠቃለያ ላይ እንደአሉት በበጀት ዓመቱ ታቅደዉ የተከናወኑ ተግባራት  ከባለፈው  ዓመት ተመሳሳይ  ወቅት ጋር ሲነፃፀር  አበረታች ዉጤቶች የተመዘገቡት  መሆኑን ነው ።

የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም በጥልቀት  መገምገም ከባለፉት አፈጻጸም  የተሻሉ አፈፃፀሞችን ለማሻሻልና መስተካከል በሚገባቸዉ አሰራሮች ላይ አቅጠጫ በማስቀመጥ ለቀጣይ ዓመት የተሻለ ዕቅድ  ለማቀድ ከማገዙም  በተጨማሪ በቀጣይ አምስት አመት ለሚከናወኑ የጤና ሥራዎች መሠረት እንደሆነ የቢሮ ኃላፊዉ ተናግረዋል።

የቢሮ ኃላፊው አክለውም በበጀት ዓመቱ በአብዛኛው ፕሮግራሞች የተመዘገቡ  ዉጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል  ከታችኛው መዋቅር  ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት  ብለዋል።

በጤናው ዘርፍ በርካታ ሥራዎች የሚሰሩ ቢሆንም የተሰሩ ሥራዎች መረጃ አጠናክሮ  ወደ ጤና የመረጃ ሲስተም ከማስገባት አኳያ ሰፊ ዉስንነቶች በመኖራቸው በቀጣይ በትኩረት  መሰራት እንደአለበት ቢሮ ኃላፊው  አሳስበዋል ።

የበጀት አስዳደርና አጠቃቀም በተመለከተ በመንግስትም ሆነ በባለድርሻ አካላት  የሚመደቡ በጀቶች አጠቃቀም ከቢሮ ጀምሮ  እስከታችኛው የጤና መዋቅር ድረስ ተፈትሾ  ማስተካከያ በሚፈልጉ አሰራሮች ላይ ማስተካከያ መደረግ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ  ተናግረዋል ።

በቢሮ የሚደረጉ የድጋፍ እና ክትትል  ሥራዎች ችግር ፈቺና ዉጤት  በሚያስመዘግብ መልኩ መሆንና ሜንተርሽፕ ላይ ማተኮር   እንደሚገባው አቶ ወልተጂ አስገንዝበዋል።

የጤና ሥራ ካለዉ የሥራ ስፋት አኳያ ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ በመሆኑ በስራ ክፍሎች መካከል  ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠል
እንዳለበት የቢሮ ሀላፊው  አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *