የክልሉን የላብራቶሪ ጥራት ለማሻሻያ የዉጫዊ ጥራት ቁጥጥር /EQA / ሥራ ማጠናከር ወሳኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ጤና ቢሮ እና ክልላዊ ላብራቶሪ ከአሶሳ ጤና ጣቢያ ጋር በዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር/EQA/ የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ
የክልሉን የላብራቶሪ ጥራት ለማሻሻያ የዉጫዊ ጥራት ቁጥጥር /EQA / ሥራ ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ነው ።
በየተቋማቱ የሚሰጠዉን የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ህሙማን ትክክለኛ የሆነ መድሀኒት እንዲያገኙ የሚያደርግ ስለሆነ የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደአለበት አቶ አለም ተናግረዋል ።
ቀደም ሲል በሁለቱ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ተገድቦ የነበረዉ የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ ወደ አሶሳ ጤና ጣቢያ መዉረዱ ማህበረሰቡ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ምክትል የቢሮ ሀላፊው አስገንዝበዋል ።
ምክትል የቢሮ ሀላፊው አክለውም የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ ይበልጥ ለማጠናከር የናሙና ቅብብሎሽ ሰንሰለት ማጠናከር ሲቻል በመሆኑ የናሙና ቅብብሎሽ ሰንሰለት ለማጠናከር የጤና ተቋማት በትኩረት መስራት እንደአለባቸዉ አሳስበዋል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ የጤና ተቋማት በላብራቶሪ አገልግሎት ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማወቅና የሚሰጠው የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።
ክልላዊ ላብራቶሪ ቀደም ሲል በወባ፣በቲቢ እና በኤች.አይ.ቨ ኤድስ በሽታዎች በመንግስትና በግል የጤና ተቋማት ላይ የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ እንደሚሰራ ከመድረኩ ለማወቅ ተችሏል ።
።

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ለማሻሻል የሚመለከታቸው አካላት አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ።ቢሮው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአሶሳ ዞን 15 ጤና ኬላዎች ለተወጣጡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በIUCD በቤተሰብ ዕቅድ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።
የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ለማሻሻል በክልሉ ዘርፌ ብዙጨተግባራት እየተከናወኑ ቢሆንም የIUCD/ሉፕ/ አገልግሎት ሲታይ በጣም አነስተኛ ነው ።
ይህን አገልግሎት ለማሻሻልና አገልግሎቱን ወደ ተጠቃሚዎች ለማድረስ አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎችን በዘርፉ ማሰልጠን አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው እንዲሰጥ መደረጉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር ገልጸዋል ።
የክልሉን የቤተሰብ ጤና አገልግሎት በተለይም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያለዉን የIUCD/ሉፕ/ አገልግሎት ለማሻሻል በዘርፉ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ማሰልጠን እና እስከ አሁን በሆስፒታሎችና በጤና ጣቢያዎች ወደ ጤና ኬላዎች አገልገሎቱን ማዉረድ መሆኑን ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል ።
ምክትል ሀላፊዉ አክለውም ሰልጣኞቹ ስልጠናው በሚገባ ተከታትለው ወደ ተቋማቸው ስመለሱ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።
በጤና ሚኒስቴር የወጣቶች፣አፍላ ወጣቶች እና የቤተሰብ ዕቅድ ዴስክ የቴክኒካል አማካሪ አቶ አስራት ሰበታ በበኩላቸው እንደሀገር የIUCE/ሉፕ / አጠቃቀም ሽፋን በተፈለገው መልኩ ባለመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠዉ በተቀመጠ ሀገራዊ ኢንሼቲቭ መሠረት አገልግሎቱን ለሚሰጡ ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጥ መደረጉን ተናግረዋል ።
IUCE/ሉፕ የቤተሰብ ዕቅድ ከጤና አንፃር ተስማም፣አንዴ ከተቀመጠእስከ አስራ አምስት አመት የሚያገለግል እና በጣም ርካሽ በመሆኑ እጅግ ተመራጭ የቤተሰብ ዕቅድ በመሆኑ ተመራጭ ነው ብለዋል።
ስልጠናው ከአሶሳ ዞን ከ8 የጤና ኬላዎች ለተወጣጡ 15 የጤና ኤክሰቴንሽን ባለሙያዎች ለተከታታይ 11 ቀን እንደሚሰጥ ከመረሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል
በካማሽ ዞን በዛይ ወረዳ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በ38 ሚሊዮን ብር የተገነባው የአምባብስ ጤና ጣቢያ የክልል፣የዞን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ተመረቀ።
የአምባብስ ጤና ጣቢያ በቀበሌዉ መገንባት የአምባቢስ እና አጎራባች የቀበሌ ነዋሪዎች ህክምና ፍለጋ ወደ ሌላ አከባቢ ከመሄድ በቅርበት ተገቢዉን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ የእናቶችንና ህፃናት ጤና ለማሻሻል የጎላ ድርሻ እንዳለዉ የዛይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑ ዴረሳ ገልጸዋል ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካማሽ ዞን ቅርንጫፍ ሥራ አስከያጅ አቶ ምስጋናዉ አምሣሉ እንዳሉት ንግድ ባንኩ የማህበረሰብ አገልግሎትን ለማጠናከር በጤና፣በትምህርት እና በአከባቢ ጥበቃ ሥራዎች የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው ይህ ዛሬ የሚመረቀዉ የጤና ጣቢያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 254 ሚሊዮን በመመደብ በ6 ክልሎች ከሚገነቡ 9 ጤና ጣቢያዎች አንዱ ነው ብለዋል።
የካማሽ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ፃፈዉ በበኩላቸው የዚህ ጤና ጣቢያ ግንባታ መንግስት የዞኑን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ያለዉን ዝግጁነት ማሳያ መሆኑን ገልፀው ለግንባታው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተ
ጂ በጋሎ የጤና ጣቢያው ግንባታው የተጀመረው በ2010 ዓ/ም ቢሆንም በመሀል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየት በ2017 ዓ/ም በድጋሚ ወደ ሥራ በመግባት እነሆ ዛሬ ለምርቃ መብቃቱን ገልፀዋል።
ጤና ጣቢያዉ ለአካባቢው ህዝብ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን እና ምቹ የስራ አካባቢን በማካተት ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ መገንባቱን የቢሮ ሀላፊዉ አስታውቋል ።
በተለይም ይህ ተቋም ለእናቶችና ሕፃናት፣ ለወጣቶች፣ ለአረጋውያን እና ለሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በመስጠት ትልቅ አሻራ ያኖራል ብለን እናምናለን ብለዋል የቢሮ ሀላፊው ።
ይህ የጤና ጣቢያ በቀበሌውና በአጎራባች ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ5000 በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት የቢሮ ሀላፊው ዛሬ የተመረቀዉ ጤና ጣቢያ በተሰጠው ስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት እንዲሰጥ በቢሮ በኩል አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ግብዓቶችና የሰው ሀይል የማሟላት ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል ።
በጤና ጣቢያዉ ምርቃ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ዛሬ የተመረቀው ጤና ጣቢያ ለህዝባችን ጤና፣ ለወደፊት ትውልድ ተስፋ እና ለማህበረሰባችን እድገት የተደረገ ታላቅ አስተዋፅኦ ነው ብለዋል።
ይህንን ፕሮጀክት ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ድጋፍ ላደረጉ ለጤና ሚ/ር ፣ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ።፣መንግስታዊ አካላት፣ ደጋፊ ተቋማት፣ መሐንዲሶች፣ ሰራተኞች እና ሁሉም አጋሮች ከልብ የመነጨ ምስጋና እንደሚገባቸው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዉ ህብረተሰቡ ለተቋሙ ተገቢዉን እንክብካቤ በማድረግ በዘለቄታዊነት አገልግሎት እንዲሰጥ የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸዉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል።
ግንባታዉ አቶ ኤርሚያስ ዲማ በተባሉ ኮንትራክተር የተሰራ መሆኑን ከመረሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።
ወቅታዊ ሪፖርት በወቅቱ ባለማቅረባቸው በ88 የግል መካከለኛ ክሊኒኮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ አስታወቀ ።
ጥራት ያለዉን የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማደረግ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ በአጋርነት የሚሰሩበትን ስርዓትን መዘርጋቱ ይታወቃል ።
ይሁን እንጂ የግል የጤና ተቋማቶች በአዋጅ ቁጥር አንቅጽ 46 በተቀመጠዉ መሠረት የጤና መረጃን በመመዘገብና ለሚመለከተዉ አካል ሪፖርት የማደረግ ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ ባለመወጣታቸዉ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ የቢሮ የምግብ ፣መድሀኒት፣ ጤና ክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ባንዞ ገልፀዋል።
እነዚህ የግል ጤና ተቋማት ከ1ወር እስከ 9 ወር በተከታታይ ለሚመለከታቸው አካል ሪፖርት ያላቀረቡ በመተከል ዞን ፣በአሶሳ ዞን እና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መካከለኛ ክሊኒኮች ሲሆኑ የተወሰደዉ እርምጃ ከማስጠንቀቂያ እስከ እገዳ ድረስ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ።
እነዚህ ተቋማት በተቀመጠው አሰራር መሠረት እስከ ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም ሪፖርት የማያቀርቡ ከሆነ የተቋማቱን ፍቃድ የመሰረዝ እርምጃዎች ሊከተሉ ስለሚችሉ ተቋማቶች ሊያስቡበት እንደሚገባው ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
በአገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ሴክተሮች የተጀመረው የሪፎርም ስራዎችን በክልሉ ጤና ቢሮ ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ። ከፊደራልና ከክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የተውጣጡ አባላት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የሪፎርም ሥራዎች ያለበት ሁኔታ ገምግሟል።
በመጀመሪያው ዙር ወደሪፎርም ስራ እንዲገቡ ከተመረጡ ተቋማት አንዱ የቤኒሻንጉል ጉሚዝ ክልል ጤና ቢሮ ሲሆን በቢሮው በባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ሥራዎች ከፊደራልና ከተለያዩ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተውጣጡ አባላት በፊደራል ደረጃ የተዘጋጀ ቼክሊስት በመያዝ የቢሮው የሪፎርም ስራ ያለበትን ደረጃ የመመልከትና፣የድጋፍና ክትትል አድርገዋል።
የቢሮው አመራሮችና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላትም የቢሮዉን የስራ እንቅስቃሴያቸውን ካቀረቡ በኋላ የድጋፍና ክትትል ቡድኑ እንደሀገር የተጀመረውን ሪፎርም ወደ ሥራ ለማስገባት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል ።
ቢሮው የስራ አካባቢን ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑ፣በጤናው ሴክተር በተለያዬ ደረጃ የሚገኙ አመራሮችን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ፣የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጅ ለመደገፍ መሰረት ልማት እየተዘረጋ መሆኑ፣ከክልል እስከ ወረዳ ተናናቢ መዋቅር እየተዘጋጀ መሆኑ፥ የጤና አገልግሎት አሰጣጡ ጥራት ያለው ለማድረግ የተለያዩ ስትራቴጅ ዶክመንቶች መዘጋጀታቸው ጠንካራ አሰራር መሆናቸውን የድጋፍና ክትትል አባላት ገልጸዋል ።
የክትትል አባላት አክለዉም እነዚህ የተጀመሩ ጠንካራ ሥራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ እና የሚቀሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና የተጠናከረ መረጃዎች ተደራጅቶ እንዲቀመጥ ምክረ ሃሳብ ተሰጥቷል ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ የተደረገው ድጋፍና ክትትል የተሰሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በአሰራር የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን ፈጥኖ ለመቅረፍ የጎላ ድርሻ ስለአለው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ከሚያዝያ 29-ግንቦት 2/2018 ዓ.ም ድረስ ቤት ለቤት የሚሰጠውን የፖሊዮ ክትባት (bOPV) ዘመቻ ስኬት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ ጥሪ አቀረቡ ።
የክልሉ ጤና ቢሮ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።
በዚህ መድረክ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ እንዳሉት የፖሊዮ በሽታ ህጻናትን ለአካል ጉዳት ብሎም ለሞት የሚዳርግ አደገኛ በሽታ መሆኑን ገልጸዋል።
በሽታውን ለመከላከል ክትባት ማስከተብ አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዘቡት ምክትል ቢሮ ሀላፊው በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በማስከተብ ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።
በዚህ ዘመቻ ከፖሊዮ ክትባት በተጨማሪ መደበኛ ክትባት ያልወሰዱ ህጻናት እንዲከተቡ፣ክትባት ጀምሮ ያቋረጡ ህጻናት በመለየት የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም የፊስቱላ ባሽታን ጨምሮ ለሎች የጤና ፕሮግራሞች በቅንጅት እንደሚሰራም ተገልጸዋል።
በዚህ ዘመቻ ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ከ220 ሺ በላይ ህጻናት ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ደግሞ በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረቱሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብራቱ በጉኖ ናቸው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤናው ዘርፍ አጋር አካላት፣ከተለያዩ ሴክተር የተወጣጡ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ለሎች ባለድርሻ አካላይ በበኩላቸው ለዘመቻው ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ!


