ካማሽ ዞን በዛይ ወረዳ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በ38 ሚሊዮን ብር የተገነባው የአምባብስ ጤና ጣቢያ የክልል፣የዞን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ተመረቀ።

በካማሽ ዞን በዛይ ወረዳ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በ38 ሚሊዮን ብር የተገነባው የአምባብስ ጤና ጣቢያ የክልል፣የዞን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ተመረቀ።

የአምባብስ ጤና ጣቢያ በቀበሌዉ መገንባት የአምባቢስ እና አጎራባች የቀበሌ ነዋሪዎች ህክምና ፍለጋ ወደ ሌላ አከባቢ ከመሄድ በቅርበት ተገቢዉን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ የእናቶችንና ህፃናት ጤና ለማሻሻል የጎላ ድርሻ እንዳለዉ የዛይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑ ዴረሳ ገልጸዋል ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካማሽ ዞን ቅርንጫፍ ሥራ አስከያጅ አቶ ምስጋናዉ አምሣሉ እንዳሉት ንግድ ባንኩ የማህበረሰብ አገልግሎትን ለማጠናከር በጤና፣በትምህርት እና በአከባቢ ጥበቃ ሥራዎች የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው ይህ ዛሬ የሚመረቀዉ የጤና ጣቢያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 254 ሚሊዮን በመመደብ በ6 ክልሎች ከሚገነቡ 9 ጤና ጣቢያዎች አንዱ ነው ብለዋል።

የካማሽ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ፃፈዉ በበኩላቸው የዚህ ጤና ጣቢያ ግንባታ መንግስት የዞኑን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ያለዉን ዝግጁነት ማሳያ መሆኑን ገልፀው ለግንባታው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተ
ጂ በጋሎ የጤና ጣቢያው ግንባታው የተጀመረው በ2010 ዓ/ም ቢሆንም በመሀል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየት በ2017 ዓ/ም በድጋሚ ወደ ሥራ በመግባት እነሆ ዛሬ ለምርቃ መብቃቱን ገልፀዋል።

ጤና ጣቢያዉ ለአካባቢው ህዝብ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን እና ምቹ የስራ አካባቢን በማካተት ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ መገንባቱን የቢሮ ሀላፊዉ አስታውቋል ።

በተለይም ይህ ተቋም ለእናቶችና ሕፃናት፣ ለወጣቶች፣ ለአረጋውያን እና ለሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በመስጠት ትልቅ አሻራ ያኖራል ብለን እናምናለን ብለዋል የቢሮ ሀላፊው ።

ይህ የጤና ጣቢያ በቀበሌውና በአጎራባች ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ5000 በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት የቢሮ ሀላፊው ዛሬ የተመረቀዉ ጤና ጣቢያ በተሰጠው ስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት እንዲሰጥ በቢሮ በኩል አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ግብዓቶችና የሰው ሀይል የማሟላት ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

በጤና ጣቢያዉ ምርቃ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ዛሬ የተመረቀው ጤና ጣቢያ ለህዝባችን ጤና፣ ለወደፊት ትውልድ ተስፋ እና ለማህበረሰባችን እድገት የተደረገ ታላቅ አስተዋፅኦ ነው ብለዋል።

ይህንን ፕሮጀክት ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ድጋፍ ላደረጉ ለጤና ሚ/ር ፣ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ።፣መንግስታዊ አካላት፣ ደጋፊ ተቋማት፣ መሐንዲሶች፣ ሰራተኞች እና ሁሉም አጋሮች ከልብ የመነጨ ምስጋና እንደሚገባቸው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዉ ህብረተሰቡ ለተቋሙ ተገቢዉን እንክብካቤ በማድረግ በዘለቄታዊነት አገልግሎት እንዲሰጥ የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸዉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል።

ግንባታዉ አቶ ኤርሚያስ ዲማ በተባሉ ኮንትራክተር የተሰራ መሆኑን ከመረሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *