በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ከሚያዝያ 29-ግንቦት 2/2018 ዓ.ም ድረስ ቤት ለቤት የሚሰጠውን የፖሊዮ ክትባት (bOPV) ዘመቻ ስኬት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ ጥሪ አቀረቡ ።
የክልሉ ጤና ቢሮ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።
በዚህ መድረክ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ እንዳሉት የፖሊዮ በሽታ ህጻናትን ለአካል ጉዳት ብሎም ለሞት የሚዳርግ አደገኛ በሽታ መሆኑን ገልጸዋል።
በሽታውን ለመከላከል ክትባት ማስከተብ አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዘቡት ምክትል ቢሮ ሀላፊው በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በማስከተብ ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ነው ያሳሰቡት።
በዚህ ዘመቻ ከፖሊዮ ክትባት በተጨማሪ መደበኛ ክትባት ያልወሰዱ ህጻናት እንዲከተቡ፣ክትባት ጀምሮ ያቋረጡ ህጻናት በመለየት የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም የፊስቱላ ባሽታን ጨምሮ ለሎች የጤና ፕሮግራሞች በቅንጅት እንደሚሰራም ተገልጸዋል።
በዚህ ዘመቻ ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ከ220 ሺ በላይ ህጻናት ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ደግሞ በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረቱሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብራቱ በጉኖ ናቸው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤናው ዘርፍ አጋር አካላት፣ከተለያዩ ሴክተር የተወጣጡ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ለሎች ባለድርሻ አካላይ በበኩላቸው ለዘመቻው ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ!
