የአለም ጤና ድርጅት በክልሉ ሊከሰቱ የሚችሉ የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስራን ለማጠናከር ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ግብአቶችን ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ በክልሉ በተለያዩ ወቅት የሚከሰቱ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከል ብሎም ምላሽ ለመስጠት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ድጋፉን የተረከቡት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር ተናግረዋል።
ይህ ግብረ ሰናይ ድርጅት የክልሉን የጤና ስርዓትን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጹት ምክትል ቢሮ ሀላፊው ለተደረገው ድጋፍ በክልሉ ጤና ቢሮ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአለም ጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት ያደረገው የህክምና ግብአት ድጋፍ መካከል የኮሌራ መከላከያ ኪት አና መድሀኒቶች እንዲሁም የወባ በሽታ መድሃኒቶችና ሌሎች ግብአቶች ይገኙበታል።
ድርጅቱ ድጋፉን ሲያደርግ ቢሮው ባቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑን በመግለፅ እንደ ክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ የወባ በሽታ ብዛት የሚከሰት በመሆኑ የመጡ መድሀኒቶችም እጥረት እንዳይከሰት የበኩላቸውን ያግዛሉ በማለት በቀጣይም እገዛው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
