የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የእናቶች ህጻናት ወጣቶች አፍላ ወጣቶችና የስርአተ ምግብ ዳይሬክቶሬት የ2018 ዓ/ም የ9 ወር አፈጻጸም ውጤታማ ነው ሲል ገለጸ፡፡

የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የእናቶች ህጻናት ወጣቶች አፍላ ወጣቶችና የስርአተ ምግብ ዳይሬክቶሬት የ2018 ዓ/ም የ9 ወር አፈጻጸም ውጤታማ ነው ሲል ገለጸ፡፡

በጤና ቢሮ የእናቶች ህጻናት ወጣቶች አፍላ ወጣቶችና የስርአተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ አብዱራሂም እንደገለጸት ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ተግባራቶች ሲገመገሙ 87% መሆኑ በቀሩት 3 ወራት ከዚህ በተሻለ ለመስራት ተነሳሽነትን የፈጠረ ነው ሲሉ ገልጸዋለል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ አገላለጽ ባለፉት 9 ወራት የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራቶች የተከናወኑ ቢሆንም እንደ አገር ብሎም እንደ ክልላችን በተፈጠረው የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ምክንያት በተፈለገ መልኩ እስከ ታችኛው የጤና መዋቅሮች ወርዶ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ለመስራት አለመቻሉን ነዉ።
ከዚህም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተረጋግቶ አለመስራት ፣ የባለሞያዎች ቁርጠኝነት ማነስ እና ልምድ ያላቸው ባለሞያዎች ከስራ መልቀቅ ስራውን በሚፈለገው ልክ መስራት አለመቻላቸውን ዳይረክተሩ ተናግረዋል ።

የጤና ስራ ትኩረት የሚፈልግና ለጤና ተቋም ብቻ የሚተው ባለመሆኑ በተለይም የእናቶች ህጻናት ጤና ልዩ ትኩረት የሚሻ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ማህበረሰቡ ከጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ሆስፒታል ባለው ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ በተዋረድ የሚገኙ የጤና ተቋማት ፣ የጤና ባለሞያዎች፣ የአመራሮች አካላትና በጤናዉ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ የድርሻቸውን በመወጣት አጋርነቱን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የእናቶች ህጻናት ወጣቶች አፍላ ወጣቶችና የስርአተ ምግብ ዳይሬክቶሬት በቤተሰብ ምጣኔ፤ በወሊድ አገልግሎት ፤ በክትባት አገልግሎት በሳንባ ምች፤የተቅማጥ በሽታ መከላከል ፤ የህጻናትና ጨቅላ ህጻናት ህክምና እንዲሁም በስርአተ ምግብ ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ አቶ አብዱልፈታ ገልጸዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *