ወቅታዊ ሪፖርት በወቅቱ ባለማቅረባቸው በ88 የግል መካከለኛ ክሊኒኮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ አስታወቀ ።
ጥራት ያለዉን የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማደረግ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ በአጋርነት የሚሰሩበትን ስርዓትን መዘርጋቱ ይታወቃል ።
ይሁን እንጂ የግል የጤና ተቋማቶች በአዋጅ ቁጥር አንቅጽ 46 በተቀመጠዉ መሠረት የጤና መረጃን በመመዘገብና ለሚመለከተዉ አካል ሪፖርት የማደረግ ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ ባለመወጣታቸዉ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ የቢሮ የምግብ ፣መድሀኒት፣ ጤና ክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ባንዞ ገልፀዋል።
እነዚህ የግል ጤና ተቋማት ከ1ወር እስከ 9 ወር በተከታታይ ለሚመለከታቸው አካል ሪፖርት ያላቀረቡ በመተከል ዞን ፣በአሶሳ ዞን እና በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መካከለኛ ክሊኒኮች ሲሆኑ የተወሰደዉ እርምጃ ከማስጠንቀቂያ እስከ እገዳ ድረስ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ።
እነዚህ ተቋማት በተቀመጠው አሰራር መሠረት እስከ ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም ሪፖርት የማያቀርቡ ከሆነ የተቋማቱን ፍቃድ የመሰረዝ እርምጃዎች ሊከተሉ ስለሚችሉ ተቋማቶች ሊያስቡበት እንደሚገባው ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
