አገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ሴክተሮች የተጀመረው የሪፎርም ስራዎችን በክልሉ ጤና ቢሮ ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ።

አገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ሴክተሮች የተጀመረው የሪፎርም ስራዎችን በክልሉ ጤና ቢሮ ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ። ከፊደራልና ከክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የተውጣጡ አባላት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የሪፎርም ሥራዎች ያለበት ሁኔታ ገምግሟል። በመጀመሪያው ዙር ወደሪፎርም ስራ እንዲገቡ ከተመረጡ ተቋማት አንዱ የቤኒሻንጉል ጉሚዝ ክልል ጤና ቢሮ ሲሆን በቢሮው በባለፉት ጊዜያት የተሰሩ ሥራዎች ከፊደራልና ከተለያዩ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተውጣጡ አባላት በፊደራል ደረጃ የተዘጋጀ ቼክሊስት በመያዝ የቢሮው የሪፎርም ስራ ያለበትን ደረጃ የመመልከትና፣የድጋፍና ክትትል አድርገዋል። የቢሮው አመራሮችና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላትም የቢሮዉን የስራ እንቅስቃሴያቸውን ካቀረቡ በኋላ የድጋፍና ክትትል ቡድኑ እንደሀገር የተጀመረውን ሪፎርም ወደ ሥራ ለማስገባት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል ። ቢሮው የስራ አካባቢን ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑ፣በጤናው ሴክተር በተለያዬ ደረጃ የሚገኙ አመራሮችን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ፣የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጅ ለመደገፍ መሰረት ልማት እየተዘረጋ መሆኑ፣ከክልል እስከ ወረዳ ተናናቢ መዋቅር እየተዘጋጀ መሆኑ፥ የጤና አገልግሎት አሰጣጡ ጥራት ያለው ለማድረግ የተለያዩ ስትራቴጅ ዶክመንቶች መዘጋጀታቸው ጠንካራ አሰራር መሆናቸውን የድጋፍና ክትትል አባላት ገልጸዋል ። የክትትል አባላት አክለዉም እነዚህ የተጀመሩ ጠንካራ ሥራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ እና የሚቀሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና የተጠናከረ መረጃዎች ተደራጅቶ እንዲቀመጥ ምክረ ሃሳብ ተሰጥቷል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ የተደረገው ድጋፍና ክትትል የተሰሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በአሰራር የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን ፈጥኖ ለመቅረፍ የጎላ ድርሻ ስለአለው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *