በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚያዚያ 16ኛ ጊዜ የሚካሄደው የአፍሪካ የክትባት ሳምንት በተሳካ መልኩ እንዲከናወን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚያዚያ 16ኛ ጊዜ የሚካሄደው የአፍሪካ የክትባት ሳምንት በተሳካ መልኩ እንዲከናወን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ።

በየአመቱ የሚከበረው ሀገር አቀፍ የክትባት ሳምንት በየአመቱ ሚያዚያ ወር በተለያዩ ፕሮግራም እንደሚከበር ይታወቃል ።

በዘንድሮ አመትም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በአሶሳ ከተማ “ለእያንዳንዱ ትውልድ ክትባቶች ይሠራሉ” መሪ ቃል ከፌደራል፣ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት ይከበራል ።

ይህ ሳምንት የተሳካ እንዲሆንና የታለመለትን ግብ እንዲመታ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ገልጸዋል ።

የአፍረካ የክትባት ሳምንት በክልላችን መከበሩ የመደበኛ የክትባት ፕሮግራም ከማጠናከር በተጨማሪ ከሌሎች ክልሎች የተሞክሮ ልዉዉጥ የሚደረግበት በመሆኑ ለፕሮግራሙ መሳካት ሁሉም መረባረብ እንደአለበት ምክትል የቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *