በአሶሳ ከተማ አስተዳደር እና በአቡራሞ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በህገ ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ የግል መካክለኛ ክልኒኮች እና መድሃኒት መደብሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

በአሶሳ ከተማ አስተዳደር እና በአቡራሞ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በህገ ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ የግል መካክለኛ ክልኒኮች እና መድሃኒት መደብሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

በግል ጤና ተቋማቶች ላይ የሚደረግ የቁጥጥርና የክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ቢሮው አስታውቋል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የምግብ ፣የመድሃኒትና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ባንዞ እንደገለጹት በአሶሳ ከተማና በአቡራሞ ወረዳ በሚገኙ የግል ጤና ተቋማት ላይ በተደረገው ቁጥጥር በህገ ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ተቋማትን በመለየት እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።

በዚህ መሰረት 2 መድሃኒት መደብሮች ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዙ እንዲሁም 3 ጤና ተቋማቶች ደግሞ ከባድ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታውቋል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው በተለይ ምንጫቸው ያልታወቁና ያልተፈቀዱ የወባ ግብአቶች ይዞ በመገኘታቸው፣የግዥ ደረሰኝ የለላቸው ግብአቶች ይዞ በመገኘታቸው እንዲሁም ባለሙያ ባልሆነ ሰው መድሃኒት መሸጥና የምርመራ አገልግሎት በመስጠት መሆናቸውንም ተገልጸዋል።

የሰረዛ እርምጃ የተወሰዱት ተቋማት በአሶሳ ከተማ የሚገኝ ሰላም መድሃኒት ቤት እና ኩርሙክ መድሃኒት መደብር እንዲሁም አርክ መካክለኛ ክሊኒክ ላይ ደግሞ የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን በአቡራሞ ወረዳ ደግሞ ንጋት መካክለኛ ክሊኒክና ዩኒቲ መድሃኒት መደብር የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋማት መሆናቸውንም ተገልጸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *