የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልዊ መንግሰት ጤና ቢሮ የሴቶች፤ወጣቶች እና ህጻናት ጉዳይ በ2018 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም በሀገር አቀፍ ደረጃ የዋንጫ መሆኑን ምክንያ በማድረግ የክልሉ ጤና ቢሮ እዉቅና ሰጠ ፡፡
የቢሮ የሴቶች፤ወጣቶች እና ህጻናት ጉዳይ ማስተባበሪያ ክፍል በክልሉ የሴቶች፤ወጣቶች እና ህጻናት ዙሪያ በ2018 ዓ.ም በተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ዉጤቶችን መስረት ባደረገ መልኩ የጤና ሚ/ር ባዘጋጀዉ አመታዊ የስራ አፈጻጸም ገምግማ መድረክ ላይ ላይ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልዊ መንግሰት ጤና ቢሮም ይህንን ሽልማት መሰረት በማድረግ ለክፍል አስተባሪሪና ለክፍሉ ሰራተኞች የእዉቅና መድረክ በማዘጋጀት እዉቅና ሰጥቷል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ እውቅናዉን የሰጡት የቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጅ በጋሎ በበጀት አመቱ በስራ ከፍሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተገኘዉ እዉቅና ለቢሮም እውቅና ነዉ ካሉ በኋላ የስራ ከፍሉ ላስመዘገበዉ ዉጤት በቢሮ በኩል እውቅና መስጠት ለቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ ነዉ ብለዋል፡፡
የስራ በስራ ክፍሉ አሁን በተገኘዉ እዉቅና ሳይኩራራ በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ቢሮ ሀላፊዉ ተናግረዋል፡፡
