
የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ዘርፈብዙ ምላሽ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት
- ለኤችአይቪ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ አና ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን በጥምር የኤችአይቪ መከላከል አገልግሎቶች ተደራሽ ማድረግ፣
- ኤችአይቪ በደማቸው ይገኛል ተብሎ የሚገመቱ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን አንዲያውቁና አስፈላጊውን ህክምናና መድሃኒት እንዲያገኙ ማድረግ፣
- የኤችአይቪ፣ቂጥኝን እና ሄፓታይትስ ከእናት ወደልጅ መተላለፋቸውን መግታት፣
- ኤች.አይ.ቪ በደማቸው እንደሚገኝ ያወቁ ሰዎች የጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እንዲወስዱና መድሃኒቱን ከሚወስዱት ውስጥም 95% የሚሆኑት በደማቸው ያለው የቫይረስ ልኬት መጠን በሚፈለገው ደረጃ እንዲወርድ ማድረግ፣
- ማግለልና መድሎ እና ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን መቀነስ
- ለዘርፈብዙ ምላሹ ማስፈጸሚያ የሚሆን ሃብት ማሰባሰብና የተገኘውን ሃብት የላቀ ውጤታማነት በሚያመጣ መልኩ መደልደልና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- የድጋፍና እንክብካቤ
