በቡለን ወረዳ እየተካሄደው የሚገኘው 5ተኛ ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ከ8 ሺ በላይ ህጻናት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የቡለን ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ነመራ ማሩ የሚመራ ታክስ ፎርስ የሁለተኛ ቀኑን ውሎን ግምገማ አካሂደዋል።
በግምገማው ላይ ዘመቻው በታቀደው ዕቅድ መሰረት እየተካሄደ ስለመሆኑ ታክስ ፎርሱ የተመለከተ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጠዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነመራ ማሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት በወረዳው የታለመው ህጻናት ተደራሽ እንዲሆኑ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።
በሁለተኛ ቀን ውሎው አጠቃላይ 2851 ህጻናት የተከተቡ መሆኑን በቀረበው ሪፖርት የተመላከተ ሲሆን ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተለይ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሉባቸው ቀበሌዎች በመለየት በልዩ ትኩረት ለመስራት አቅጣጫ ተቀምጧል።
ለክትባቱ ስኬት PUI የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ በተለይ የግብአት እንዲሁም ሙያዊ እገዛ በቅርበት በመከታተልና እገዛ እያደረገ መሆኑን ተገልጸዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ባደረገው ቅኝት ክትባቱ በተያዘው ዕቅድ እየተካሄደ ስለመሆኑን ለመገንዝብ ተችለዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ!
