ከመጋቢት 18_21/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ለ5ተኛ ዙር እየተሰጠ ያለዉ የፓሊዮ ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በሁለተኛ ቀኑ ከ52,996 በላይ ህፃናት መከተባቸዉን የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግሰት ጤና ቢሮ ገለፀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ በክልሉ በ23 ወረዳዎች እና በ4 የስደተኞች መጠሊያ ካምፕ የተጀመረው የፖሊዩ ክትባት ዘመቻ በ2ኛ ቀኑ ከ52,996 በላይ ህፃናት መከተባቸዉን ገልፀዋል።
በዛሬዉ ዕለት 458 ቡድኖች ባደረጉት ሪፖርት 99 በመቶ ህፃናት መከተብ የተቻለ መሆኑን የገለፁት አቶ አለም እሰከ 2ኛ ቀን 141,748 ሰዎች ሰለክትባቱ መረጃ ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል ።
እስከአሁን በተደረገው ሂደት 87,046 ቤቶችም መጎብኘታቸውን አቶ አለም ተናግረዉ በቀሪ ቀናት ዉስጥ ያልተደረሱ አከባቢዎችን ለመድረስ በትኩረት መሠራት እንዳለበት ገልፀዋል ።
አቶ አለም አክለውም ከፖሊዮ ዘመቻ ጋር በቅንጅት የሚሰጡ የጤና ፕሮግራሞች አቀናጅቶ ከመስራት የተጣራ እና የተናበበ ሪፖርት ያለማቅረብ ሥራዎች በቀጣይ መስተካከል አለበት ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዘመቻው ሂደት በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች በታክስ ፎርስ እየተገመገመ መሆኑን የዕለት ዉሎ ሪፖርት ያመላክታል ።
