ከመጋቢት 18_21/2018 ዓ.ም ጀምሮ 5ተኛ ዙር የፓሊዮ ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና ምላሽ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬት አቶ መብራቱ በጉኖ በክልሉ ከመጋቢት 18_21/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት ለሚካሄደው የፖሊዮ ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቋል ብለዋል።
ዘመቻዉ ለማስተባበር ከቢሮ፣ከዞን እንዲሁም በጤናዉ ዘርፍ ላይ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የተመደቡ ባለሙያዎች እና ተሸከሪካሪዎች ከነገ ጀምሮ በተመደቡበት ወረዳ በመገኘት ሥራ እንደሚጀምሩ አቶ መብራቱ ገልፀዋል ።
ይህን ዘመቻ ዉጤታማ ለማድረግ የተመደቡ ባለሙያዎች ከታችኛውን የጤና መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ለዘመቻው ዉጤታማነት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
አቶ መብራቱ አክለውም ዘመቻው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በዘመቻው ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች በወቅት ለመፍታት የዘመቻው ሂደት በየቀኑ በታክስ ፎርስ መገምገም እንዳለበት ገልፀው ይህንን ሥራ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት ሚና የጎላ ነው ብለዋል።
