ከመጋቢት 18_21/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ለ5ተኛ ዙር የሚሰጠዉ የፓሊዮ ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ የክልልና የአሶሳ ከተማ አመራሮች እንዲሁም በጤናዉ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአሶሳ ከተማ በይፋ ተጀመረ።
ዘመቻውን ያስጀመሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ ክትባት በፖሊዮ ቫይረስ በህፃናት ላይ የሚከሰት ከአካል ጉዳት የሚከላከል በመሆኑ መላዉ ማህበረሰብ ህፃናትን በማስከተብና ለክትባቱ መሳካትም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል።
ዘመቻው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በየደረጃዉ ያሉ የአመራር አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ በመሳኝ በመሆኑ የአመራር አካላት የዘመቻዉን ሂደት በመከታተል በዘመቻው ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች በወቅት ለመፍታት በየቀኑ በታክስ ፎርስ ዘመቻዉን መገምገም እንዳለባቸው ጠይቀዋል።
የአሶሳ ከተማ ጤና መመሪያ ሀላፊ ሲስተር ስቱ አልበሽር በበኩላቸው ክትባቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በመምሪያው በኩል አስፈላጊው የሆነ የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
በዘመቻው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢኒጅነር ፍቃዱ ተሰማ ጨምሮ ከጤና ቢሮ፣ከአሶሳ ዞን ጤና መምሪያ፣ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ላይ የሚ
