Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ራዕይ

• ጤናማ፣ አምራችና የበለፀገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት፣

ተልዕኮ

•ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የጤና አገልግሎቶችን በማቅረብ እና በመቆጣጠር የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት ማሻሻል፣

እሴቶች

    • ቅድሚያ ለህብረተሰብ
    • ታማኝነት፣ ሐቀኝነት
    • ግልፅነት፣ ተጠያቂነት፣ ምስጢራዊነት
    • አለማዳላት፣
    • ህግን ማክበር፣
    • አርዓያ መሆን፣
    • ትብብር፣
    • ሙያዊነት፣
    • ለውጥ/ፈጠራ፣
    • ርህራሄ፣

መርሆዎች

• ግልፅነትና ተጠያቂነት
• ፍትሃዊነት እና ርህራሄ
• አጋርነት እና ትብብር
• ጥራት እና ልህቀት
• አሳታፊ እና ባለቤትነት
• ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና ህግን ማክበር
• ዘላቂነት እና በራስ መተማመን

አጠቃላይ ዓላማዎች

የሁለተኛው የጤናዉ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽ እቅድ ዋናው ዓላማ “ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በማጎልበት የመላውን ህብረተሰብና የሁሉንም እድሜ ክፍል ደህንነት ማረጋገጥ” ነው፡፡ ይህንን ዋና ዓላማ ለማሳካት የሁለተኛው የትራንስፎርሜሽ እቅድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተጨማሪ ዝርዝር ዓላማዎችን አካቷል፡-

i. የሕብረተሰቡ የጤና ሁኔታ ማሻሻል፣
ii. ሁሉ-አቀፍ የጤና ሽፋንን እውን ማድረግ፣
iii. ህብረተሰቡን ከድንገተኛ የጤና አደጋዎች መጠበቅ፣
iv. አባወራ/እማወራዎች (ቤተሰቦችን) ትራንስፎርም ማድረግ፣
v. የጤና ስርዓት ምላሽ አሰጣጥን ማሻሻል፣