Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ጥብቅ ማስታወቂያ
Posted On: May 06, 2020

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚትገኙ የሶስቱም ዞንን ጤና መምሪያ ሀላፊዎች ፣የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሀላፊዎች ፣ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊዎች ፣ ለሆስፒታል ሥራ አስከያጆች ፣ ለሁሉም የጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሀላፊዎች በሙሉ

(ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም )የእናቶችንና የህጻናት ሞት ለመቅረፍ በሁሉም የጤና ተቋማት አንቡላሶች በመመደብ ለእናቶች ጤና መሻሻል በነፃ አገልግሎት እንድሰጡ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል ።

ይሁን እንጅ አንቡላንሶቹ ከታለመላቸው አላማ ዉጭ ሲውሉ እንደነበረ በተለያዬ አጋጣሚዎች እና በተደረጉ የሥራ ግምገማዎች ለማወቅ ተችሏል

ይሁን እንጅ እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎችን በክልሉ እጠናክሮ ማስቀጥል እና የእናቶቸ እና የህጻናት ሞት ለመቀነስ የክልሉ መንንግት ያደረገዉን የገንዘብ ድጋፍ ጨምሮ በዘንድሮ አመት 40 አንቡላሶች ለሁሉም የጤና ተቋማት እንድደርሱ ተደርጓል ።

ሁሉም አንቡላንሶች ለእናቶች ጤና እና ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላክል ሥራ እንድውሉ እያሳሰብነ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር እስከ ሚቻልበት ድረስ አንድ አምቡላንስ በቋሚነት ለህብረተሰብ ጤና ቁጥጥር /ቢሮትT/ ክፍል እንድሰጥ በጥብቅ እያሳሰብን ከላይ የተገለፁ ተቋማት እና በየደረጃ የምትገኙ የመስተዳድር አካላት ለተግባራዊነቱ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ እንገልፃለን ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ

Image