Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በ2,494,244 ብር የሚገመት ወጪ የተጀመረዉ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡ (አሶሳ ነሀሴ 15/2017 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት አመት በ2,494,244 ብር የሚገመቱ የተለያዩ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመሥራት በታቀደዉ መሰረት በካማሽ ዞን ከከማሽ ለ1,702,744 አቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን የሁለት አዲስ ቤት ግንባታ፣ የሁለት ነባር ቤቶች ዕድሳት እየተካሄደ ሲሆን ፣በ528,500 ለ100 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እገዛ እና ለ100 አረጋዊያንና አቅመ ደካማ ሰዎች የምግብ የፍጆታ እቃዎች የማቅብ ስራ ተሰርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ በሚገኙ የመንግሰትና የግል የጤና ተቋማት ተላላፊ እና ታላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነጻ ምርመራና ህክና እየተሰጠ ይገኛል ተብሏል፡፡ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት እስከ ጳጉሜ ወር የሚቀጥል ስለሆነ ህብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆነም ጥሪ ቀርቧል፡፡