Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ

 መግቢያ

ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ መንግስት የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎችን ነድፎ ለተፈፃሚነታቸው ሠፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከነዚህ ፖሊሲዎች መካከል አንዱ የጤና ፖሊሲ ነው።

በዚህም መሰረት በአራት የጤና ዘርፍ ልማት እቅድ ዘመናት እንዲሁም የመጀመሪያ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማዘጋጀት እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ አራቱን የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ቀርጻ ተግባራዊ ስታደረግ ቆይታለች፡፡ በክልላችንም የአገሪቱን የጤና ዘርፍ አስተቃቀድ ሂደት በመከተል የረጅም ጊዜ እቅዶችን በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ የክልሉን ህብረተሰብ የጤና ልማት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ጤናው የተጠበቀ፣ ጠንካራና አምራች ህብረተሰብ ለመፍጠር መከላከልን መሠረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተቀርፆ ወደ ተግባር በመገባቱ በርካታ መልካም ውጤቶችን ማስመዘገብ ተችሏል። በተያዘዉ አቅጣጫ መሠረት ይህንኑ እዉን ለማድረግና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የእናቶችና ህፃናት ጤና ማሻሻል፣ የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር (የወባ፣ ቲቢ፣ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ…ወዘተ)፣ የመሠረተ ጤና ተቋማት ግንባታ ማስፋፋት፣ በጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች እንዲሁም በፈውስ ህክምናና ተሃድሶ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመፈጸም አስፈላጊው ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

በባለፉት 30 አመታት በክልሉ አልፎ አልፎ በከተሞች አከባቢ የነበሩ የጤና ተቋማት ህብረተሰቡ በሚገኝበት አከባቢዎች ለማዳረስ በተከናወኑት ተግባራት በአሁኑ ሰዓት 55 የጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ፤2 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስታሎች፤4 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፤13 የቀዶ ህክምና ማዕከላት፤2 የደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤቶች 403 በላይ የጤና ኬላዎች፤አንድ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አንድ ከልላዊ ላብራቶሪ  ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስተጥ ላይ ስሆኑ አንድ የመጀመሪ ደረጃ ሆስፒታል ጨምሮ በርካታ የጤና ተቋማት በግንበታ ሂደት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ተግባራት በመከናወናቸዉ በክልሉ አልፎ አልፎ በወረርሽን መልክ ይከሰቱ የነበሩ በሽታ ለመከላከል ከመቻሉም በላይ የእናቶችንን የህጻናት ሞት ለመቅረፍ ከመቻሉም በላይ ከዛሬ 30 አመት በፊት 7 በመቶ የነበረዉ የክልሉ የጤና ሽፋን ከ94 በመቶ በላይ ለማደርስ ተችሏል ፡፡ 

በቀጣይ ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም እንዲሁም እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚደረግ ክልላዊ የጤናው ዘርፍ የለውጥ እቅድ ተዘጋጅቶ በዚህ ሰነድ ላይ የተመላከተ ሲሆን እቅዱ አገራዊ የ10 አመት የጤናው ዘርፍ ፍኖተ ካርታን እና የቀጣይ 5 አመታት የጤናው ዘርፍ የለውጥ እቅድን መነሻ በማድረግና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

 

 

በጤና ጥበቃ ቢሮ  ያሉ ፕሮጀክቶች

1.-አዳስ የጤና ተቋማት ግንባታና ማስፋፋት

 

በጤና ጥበቃ ቢሮ ያሉ ፕሮግራሞች

  • የክትባት ፕሮግራም
  • የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም
  • የእናቶች ጤና ፕሮግራም
  • የስነ ተዋልዶ ጤና ፕሮግራም
  • የበተሰብ ዕቅድ ፕሮግራም
  • የህጻናትን ጨቅላ ህጻናት ፕሮግራም
  • የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም
  • የሀይጅንና አከባቢ አጠባበቅ ፕሮግራም
  • የቲቪና ስጋ ደዌ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም
  • ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም
  • ትኩረት የሚሹ ሀረራማ በሽታዎች  መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም
  • የጤና አተባበቅና የባህረ ለዉጥ ተግባቦት ፕሮግራም
  • የዘርፌ ብዙ ምልሽ ኤች አይቨ ኤድስ መከላከልንና መቆጣጠር ፕሮግራም