Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

media network

በ2017 ዓ.ም ጤናው ዘርፍ ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበረ ተገለጸ። የክልሉ ጤና ቢሮ አመታዊ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሙያዎች የምክክር መድረክ አካሂደዋል። ዓመታዊ የምክክር መድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ እንዳሉት ለጤናው ዘርፍ መሻሻል የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። በተለይ ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የገለጹት አቶ አለም ይህንን አጠናክሮ እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል ። በክልሉ ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዋጮ ዋቡልቾ በበኩላቸው የጤናው ዘርፍ የልማት ዕቅዶችን ከዳር ለማድረስ የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ የጎላ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል ። ከ2008 ዓም ጀምሮ የተቋቋመው ይህ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ፎረም በተጠናከረና በተቀናጀ አኳሃን ማስኬድ እንደሚገባም አቶ ዋጮ ጠቁመዋል። ዓመታዊ የምክክር መድረኩ ላይ ወቅታዊ የወባ በሽታ፣የኤም ፖክስ እንዲሁም የአደጋ ጊዜ የተግባቦት ስልት ላይ የመረጃ ልውውጥ ከመደረጉም ባሻገር የሴክተር መስሪያ ቤትና የወረዳዎች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በምክክር መድረኩ ላይ አገራዊና ክልላዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ የክልልና የወረዳ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ተገኝቷል። የክልሉ ጤና ቢሮ!