Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የአይን ቆብ መቀልበስ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የአይን ቆብ መቀልበስ በሽታ በጊዜው ካልታከሙ ማህበረሰቡ ላይ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግር ያስከትል ተባለ፡፡ የአይን ቆብ መቀልበስ በሽታ በቀላሉ በህክምና መዳን የሚችል በሽታ ሲሆን በወቅቱ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ እና ህክምና ባለማድረግ የተነሳ በርካታ ዜጎችን ለችግር እየዳረገ ይገኛል ። ህብረተሰቡ በአግባቡ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራና ህክምና ካልተደረገ ከፍተኛ የሆነ ህመምና ስቃይ ከማድረሱ ባሻገር የአይን እይታ መሰወር እንደሚያመጣ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ ባለድረሻ አካላት ጋር በመሆን የአይን ቆብ በሽታ ያለባቸዉን ወገኖች የመለየት እና የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ። በዚሁ መረሠት Amref Health Africa Assosa project የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በአሶሳ ዞን ኡራ ወረዳ ስር በሚገኙ ቀበሌዎች የአይን ቆብ መቀልበስ ችግር ላለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የልየታ ሥራና የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው ። የAmref Health Africa Assosa project አስተባበሪ ወ/ሮ ሽጉጤ አለነ ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት በበርካታ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ላይ የአይን ቆብ መቀልበስ ችግር ላለባቸው ሰዎች ቅድመ ልየታና የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷቸው ከበሽታው ህመምና ስቃይ መዳን እንደቻሉ ተናግረዋል ፡፡ በዚህ ዙር በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን የልየታ ሥራ በመስራት ህመሙ ላለባቸው ሰዎች የአይን ቆብ መቀልበስ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት እንደሚቀጥ ጭምር ገልጸዋል ፡፡ ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም