Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና ተቋማት ብክለት አወጋገድ

በጤና ተቋማት የሚከሰተውን ብክሌት መከላከል እና መቆጣጠር በጤና ተቋማት የሚሰጠዉን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተገለፀ ። የክልሉ ጤና ቢሮ ከአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ከመንጌና በቡልድግሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ለተወጣጡ የሚመለከታቸው አካላት በብክሌት መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል። በጤና ተቋማት የሚከሰተውን ብክሌት መከላከል እና መቆጣጠር በጤና ተቋማት የሚሰጠዉን የጤና የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የጎላ ድርሻ ስለአለው በዘርፉ ለሚሰሩ የሆስፒታል ባለሙያዎችና የአመራር አካላት በክልሉ ሥራ አመራር ተሰጥቷል ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የክሊኒካል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አብዱራሀማን አማኔላ የስልጠናው ዋና ዓላማ በክልሉ በሆስፒታሎች ያለዉ የብክሌት መከላከል እና መቆጣጠር ሥራዎች በተፈለገዉ መልኩ ባለመሆኑ ፕሮግራሙን ለማነቃቃት እና ወደ ሥራ ለማስገባት የተዘጋጀ የማነቃቂያ መድረክ ነዉ ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሆስፒታሎች መካከል የተሞክሮ ልዉዉጥ ለማድረግ ከማገዙም በላይ ሆስፒታሎች ያለውን የብክሌት መከላከል ሥራዎች ነባራዊ ሁኔታ እንዲረዱ ያደርጋል ብሏል ። ይህን ሥራ ዉጤታማ ለማድረግ በየተቋማቱ የሚሰሩ ሥራዎች በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት መቅረብ እንደአለበት ተወካዩ ገልጸዋል ። በመድረኩ የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በብክሌት መከላከል እና መቆጣጠር ዙሪያ የተሰሩ ሥራዎች እና ያጋጠሙ ችገሮች ቀርበዉ የተወያዩበት ሥሆን በጤና ተቋማት የሚከሰተውን ብክለት ለመከላከል ሥራ ለፅዳት ሠራተኞች ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም የህክምና ክፍል ሀላፊነት እንዳለበት በዉይይት ወቅት ተነስቷል ። በጤና ተቋማት የሚከሰቱ ብክለት ለመከላከል የንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶች በወቅቱ ተገዝተው መቅረብ እንደአለባቸዉ የዉይይቱ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል ። ነሀሴ 6/2017 ዓ.ም