Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና መረጃ ስርዓት ማጠናከር የጤና አገልግሎት ስርዓተን ለማሻሻል የጎላ ድርሻ አለዉ ተባለ

በጤናው ዘርፍ የመረጃ አያያዝና ጥራትን ማሻሻል ጥራት ያለዉን የጤና አገልግሎት ለመስጠት የጎላ ድርሻ እንዳለዉ ተገለፀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በጤና መረጃ አያያዝ ዙሪያ ከጤና ተቋማት ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ። ከቢሮ ጀምሮ እስከታችኛው የጤና ተቋማት ጥራት ያለዉ የጤና መረጃ ሥርዓት በመዘርጋት ወጥ የሆነ እና የተናበበ የጤና መረጃ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት እንደሆነ ይታወቃል ። እነዚህን የተጀመሩ ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ከመረጃ አያያዝ ጥራት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የአቅም ክፍተቶችን ለመቅረፍ በተግባር ልምምድ የተደገፈ የአቅም ስልጠና ለማዘጋጀት መቻሉን በክልሉ ጤና ቢሮ ዳታ ማናጅመንት ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደረጀ ሮባ ገልጸዋል ። ስልጠናው የጤና ተቋማትን የጤና መረጃ አያያዝን በማዘመን በጤና ተቋማት የሚሰጠዉን የጤና አገልግሎት ጥራት ከማረጋገጡ በተጨማሪ መረጃን ለውሳኔ ለመጠቀም እንደሚረዳ አቶ ደረጀ ገልፀዋል። ስልጠናዉ የተለያዩ ሶፍት ዌሮች በመጠቀም የሚሰጥ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ያለዉን መረጃ ወደ ዲጂታል መረጃ ለማሸጋገር ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አቶ ደረጀ ተናግረዋል ። አቶ ደረጀ አክለውም ስልጠና የመረጃ ሥርዓትን ከማዘመን ባሻገር የመረጃ ልዉዉጥ ሥርዓትን የሚያቀል በመሆኑ ስልጣኞቹ ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ በመከታተል ወደ ተቋማቸው ስመለስ ተግባራዊ ማድረግ እንደአለባቸዉ አቶ ደረጀ አሳስበዋል ። ይህ ስልጠና ከተለያዩ የጤና ተቋማት ለተወጣጡ 40 ሰዎች ስልጠና የተሰጠ ሥሆን በዚህ ዙር ከጤና ጣቢያ እና ከሆስፒታል ለተወጣጡ 40 ባለሙያዎች በዳታ ጥራት ፣ቁጥጥር እና አያያዝ በሚጠቅሙ ሶፊት ወሮች ላይ ያተኮረ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል ። ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም