Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

winter voulter servuce

የማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ ጤ/ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የጤናዉ ዘርፍ የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ አሰጀመረ። የወረዳው ጤና ጽ/ቤት የጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ያስጀመረዉ በወረዳው በሚገኙ 3 የጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ሲሆን በፕሮግራሙ የፅዳት ዘመቻ ፣የደም ግፊት ምርመራ፣የስኳር ምርመራ፣የHIV/AIDS ምክር እና ምርመራ፣የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና የልዬታ ሥራዎች ተሰርቷል ። እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎች እስከ ፕሮግራሙ ፍፃሜ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በነፃ የሚሰጡ በመሆኑ ማህበረሰቡ ይህን አዉቆ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆንም ጥሪ ቀርቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በወምበራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል''በመትከል ማንሰራራት''የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሄዷል ። በወረዳው ''በመትከል ማንሰራራት''የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክሮ ቀጥሏል። የወምበራ ሆስፒታል የአስተዳደር ሰራተኞችና የህክምና ባለሙያዎች በሆስፒታሉ ውስጥ ችግኝ በመተከል አሻራቸውን አሳርፈዋል። ከዚህም በተጨማሪ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የምርመራ እና የምክር አገልግሎትም በሆስፒታሉ እየተሰጠ መሆኑን የዕለት ዉሎ ሪፖርት ያመላክታል ። ሐምሌ 22/2017ዓ.ም