Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የአሶሳ ከተማ ጤና ጣቢያ ዉይይት

የአሶሳ ከተማ ጤና ጣቢያ የአገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ ቢሆንም አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ግብዓቶች ጉዳይ ሊተሰብበት ይገባል ተባለ። ከጤና ቢሮና ከጤና ሚኒስቴር የተውጣጣ ቡድን የጤና ጣቢያውን የአገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋውሮ ተመልክቷል ። የፌዴራል ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የጤና ሚ/ር ተወካይ ወ/ሮ ላምሮት አንዱዓለም የጤና ጣቢያውን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ከተመለከቱ በኋላ እንደአሉት የጤና ጣቢያው የአገልግሎት አሰጣጥና የጤና ባለሙያዎች የሥራ ተነሳሽነት እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ነው ። በተለይም እንደሀገር እየተነሳ ያለዉን የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ማለትም የባለሙያ የደንብ ልብስ፣የትርፍ ጊዜ ክፍያ እና የተገላጭነት ክፍያዎች በወቅቱ እየተከፈሉ መሆናቸው ለሌሎች ተቋማት በተሞክሮነት የሚቀርብ መሆኑን ወ/ሮ ላምሮት ገልጸዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም በበኩላቸው የአሶሳ ከተማ ጤና ጣቢያ እየተከናወኑ ያሉ የተሻሉ አፈጻጸሞች አጠናክሮ ለማሰቀጥልና መሻሻል የሚገባቸውን ተግዳሮቶች ለማሻሻል ጤና ጣቢያው ለሚያደርጋቸው ተግባራት ሁሉ የጤና ቢሮ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።