Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና ባለሙያዎች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ

በጤና ባለሙያዎች የሚነሱ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች የጤና ሚ/ር ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን የፌዴራል ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ያምሮት አንዱአለም ገለፁ ። የፌዴራል ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የጤና ሚ/ር ወክለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገኙት ወ/ሮ ያምሮት አንዱአለም ከጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ጋር በወቅታዊ የጤና ሁኔታዎች ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት የጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸው የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ተገቢነት ያላቸው ጥያቄዎች በመሆናቸው የጤና ሚ/ር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ። የቀረበው የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች በፌዴራል መንግሥትና በክልል መንግስታት እንዲሁም በጤና ተቋማት በራሳቸው የሚፈቱ በመሆናቸው ችገሮች እስክፈቱ ድረስ የጤና ባለሙያዎች የጤና ባለሙያ ስነ ምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው ወ/ሮ ያምሮት ጠይቋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በበኩላቸው በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚመላለሱ አሉባልታዎች ሳይረበሹ መደበኛ ሥራቸዉን በተገቢዉ ሁኔታ በመስራት ላይ በመሆናቸዉ ያላቸዉን ልባዊ አክብሮት ገልፀዉ በባለሙያዎች የተነሱ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ለመመለስ የተነሱ ጥያቄዎች በመለየት በክልሉ አቅም መመለስ የሚገባቸዉን በሂደት ለመመለስ ቢሮው በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል ። ግንቦት 12/2017 ዓ.ም