Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የካማሽ ሆስፒታል ጉብኝት

የካማሽ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ለማሻሻል አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ ። (12/9/2017 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ የሆስፒታሉን የሥራ እንቅስቃሴ ተጎብኝቷል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ የሆስፒታሉን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ከጎበኙ በኋላ የካማሽ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተደረጉ ያሉ ሥራዎች አበረታች በመሆኑ የበለጠ ለማሳለጥ በቢሮ በኩል አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግ ነው ። በተለይም የሶላር ተከላ ሲጠናቅ ሚኒ የደም ባንክ የማስጀመር፣የፋርማሲ ክፍል ተስተካክሎ ኦዲተብል ፋርማሲ (APTS) እንዲጀምሩና ብልሸት ያጋጠማቸውን የህክምና እቃዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ተጠግኖ ወደ ሥራ እንዲገባ ይደረጋል ብለዋል። የቢሮ ሀላፊዉ አክለውም በቀይ መስቀል ማህበር ድጋፍ በተከላ ላይ የሚገኘዉ ሶላር ሲጠናቀቅ በሆሰፒታሉ ያለው በመብራት ችግረ እንደሚቀርፍና ሪፈረ የሚደርጉትን ህሙማን ቁጥር እንደሚቀንስ ገልጸዋል ። በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ም/ጤና ቢሮ ሀላፊ አለም ደበሎ፣የካማሽ ዞን አስተዳደሪ፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች የዞኑ አመራሮች ጨምሮ ተገኝቶበታል ።