Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የብልህ ጅምር ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተቀናጀ የብልህ ጅምር የጤና አገልግሎት ማስፋፊያ ክልላዊ የማስጀሪያ ፕሮግራም ተካሄደ ። በጤና ሚኒስቴር፣በPSIና በቤተሰብ ጤና መምሪያ በጋራ የተጀመረው የተቀናጀ የብልህ ጅምር የጤና አገልግሎት ፕሮግራም በክልሉ ለቀጣይ 3 አመታት በክልሉ ሁሉም የክልሉ ወረዳዎች የሚሰራ ፕሮግራም ነው ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ እንዳሉት የዚህ ፕሮግራም በክልሉ ተግባራዊ መደረጉ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን ጤና ከማሻሻሉ በተጨማሪ የክልሉን የቤተሰብ ዕቅድ ሽፋን ከፍ የሚያደረግ በመሆኑ ለፕሮግራሙ መሳካት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደአለባዉ ገልጸዋል ። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለፕሮግራሙ ሥራዎች መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ቃል ገብተዋል ። በማስጀሪያ ፕሮግራም ላይ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ፊልጶስን ጨምሮ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤት የቢሮ ሀላፊዎች፣ምክትል የቢሮ ሀላፊዎች፣የጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የመምሪያ ሀላፊዎች፣ከጤና ሚ/ር ፣ከPSI፣ከኢትዮጵያ የቤተሰብ መምሪያ፣ የተለያዩ የወጣቶችና የሴቶችአደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት አባቶችና ከክልል፣ከዞን፣ከከተማ አስተዳደርና ከወረዳ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ። ግንቦት 8/2017ዓ.ም