Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የኩፍኝ ክትባት

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁሉም አከባቢዎች ከግንቦት 6-15/2017 ዓ.ም እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባትና ሌሎች የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ዘመቻ እስከ ሁለተኛ ቀን የተሰሩ ሥራዎች አበረታች ቢሆንም አሁንም ትኩረት የሚሹ ወረዳዎች መኖራቸዉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ። (7/9/2017ዓ.ም) የክልሉ ታክስ ፎርስ የዘመቻውን የሁለት ቀን ዉሎ ገምግሟል ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፡ጤና ቢሮ የእናቶች፣ወጣቶች፣ህፃናትና ሥርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ አብዱራሂም በዕለታዊ የዉሎ ግምገማ ላይ እንደአሉት ዘመቻው በአብዛኛው ወረዳዎች የተጀመረ ቢሆንም አሁንም በተፈለገው መልኩ ወደ ሥራ ያልገቡ ወረዳዎች በመኖራቸው ልዩ ትኩረት ያሻል ብለዋል። በተለይም ለመድረስ አስቸጋሪ የሆኑ አከባቢዎችን ለመድረስ ወረዳዎች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ዘመቻውን ማስጀመር እንደአለበት የገለፁት ዳይሬክተሩ እስከአሁን መረጃ አጠናክሮ ያላስገቡ ወረዳዎች ዕለታዊ መረጃ አጠናክሮ በየቀኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ከክልልና ከዞን የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮች በበኩላቸው በየዕለቱ ዘመቻውን በመገምገም ለዘመቻው ለመሳካት ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል ። ዘመቻው ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ሲሆን በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ 40,744 ህፃናት የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት የወሰዱ ሥሆን ለ31,964 ህፃናት የምግብ እጥረት ልዬታ ተደርጓል ። ለ20,328 የአንጀት ጥገኛ ትላትል መድሀኒት ዕደላና የኮቭዲ 19 ክትባት ለ173 ሰዎች ክትባት የተሰጠ ሥሆን፣56 የታመሙ ህፃናት የመለየትና 5 ሰዎች የፌስቱላ ልዬታ ተደርጓል ። እስከአሁን በተደረገው ዘመቻ የመንጌ ወረዳ አፈጻጸም የተሻለ ሁኖ መመዝገቡን ከዕለት ዉሎ ግምገማ ለማወቅ ተችሏል ።