Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የፈጣን ሱፐርቪዥን ሪፖርት ግምገማ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ በሁሉም ወረዳዎች የተካሄደው ፈጣን ድጋፍዊ ጉብኝት የተለዮ ክፍተቶች ለመፍታት እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት አቅዶ መስራት እንደአለበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አሳሰቡ ። (5/9/2017 ዓ.ም) በከሰልሉ በተደረገው ፈጣን ድጋፋዊ ጉብኝት የተከናወኑ ተግባራት ተገምግሟል። የጤና መድህን ሥራንና መደበኛ የጤና ሥራዎችን ለማጠናከር ከቢሮ የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ፈጣን ድጋፋዊ ጉብኝት መደረጉ ይታወቃል ። በተደረገው ፈጣን ድጋፋዊ ጉብኝት የጤና መድህን በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ አዲስ አባላት የማፍራትና የነባር አባላት እድሳት ላይ የተደረጉ የድጋፍና የክትትል ሥራዎች ዉጤታማ ቢሆንም አሁንም ልዩ ትኩረት የሚሹ ወረዳዎች መኖራቸውን አቶ ወልተጅ ገልጸዋል ። ይህ በእንዲህ እንደአለ ሌሎች መደበኛ የጤና ሥራዎችን ለማጠናከር በቡድኑ የተሰሩ ሥራዎች፣የተለዩ ክፍተቶችና የተቀመጡ አቅጣጫ አበረታች ነው ያሉት ሀላፊዉ እነዚህ የተለዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት ሥራዎችን በዕቅድ በማካተት ከታችኛውን መዋቅር ጋር በመቀናጀት መስራት እንደአለባቸዉ አቶ ወልተጂ ገልጸዋል ።