Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የዘመቻ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁሉም አከባቢዎች ከግንቦት 6-15/2017 ዓ.ም የሚሰጠው የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባትና ሌሎች የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ። (5/9/2017 ዓ.ም) የዘመቻው ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በተገኙበት ተገምግሟል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በዉይይት መድረኩ ላይ እንዳሉት በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ከግንቦት 6-15/2017 ዓ.ም የሚሰጠው የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባትና ሌሎች የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ዘመቻ ለማካሄድ የተደረጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አበረታች በመሆናቸዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንደአለበት ነው ። ዘመቻው ዉጤታማ የሚሆነው በቅድመ ዝግጅት ወቅት በተሰሩ ሥራዎች ብቻ ባለመሆኑ ከክልልና ከዞን የታችኛውን መዋቅር ለመደገፍ የተመደቡ አካላት ከታችኛው መዋቅር ጋር በቅንጅት በመስራት ለዘመቻው ዉጤታማነት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው ብለዋል ምክትል ሀላፊው ። አቶ አብዱልሙኒየም አክለውም በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት የዘመቻ ሥራዉን በመምራት የዘመቻውን አፈጻጸም በዕለቱ በመገምገም ለዘመቻው መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደአለባቸዉ አስገንዝበዋል ። ዘመቻው ግንቦት 6/9/2017 ዓ.ም ከክልል ጀምሮ በሁሉም ዞኖች፣ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች የሚጀምር ስለሆ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላትና በጤናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በማሰጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ማስጀመር እንደሚገባቸው ጠይቀዋል ።