Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የክትባት

በክልላቸን የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ከግንቦት 6-15/2017 ዓ/ም በሁሉም አካባቢዎች እድሜያቸው ከ9 ወር እስከ 5 አመት ለሆኑ ህጻናት በሁሉም የጤና ተቋማትና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ይሰጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 1. ምንም ክትባት ላልጀመሩ እንዲሁም ጀምረው ላቋረጡ ህጻናት ክትባት መስጠት 2. የታመሙ ህጻናት ልየታ ማካሄድ 3. የአጣዳፊ የምግብ እጥረት ያለባቸውን የመለየት 4. የአንጀት ጥገኛ ትላትል ህክምና ክኒን እና የቫይታሚን ኤ ጠብታ መስጠት 5. ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግር ያለባቸውን እናቶች የመለየት እንዲሁም 6. የኮቪድ -19 ክትባት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ወላጆች /አሳዳጊዎች/ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን ወደ ጤና ተቋም ወይም ወደ ጊዜያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች በመዉሰድ ክትባት እንዲወስዱ እና የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚም እንዲሆኑ እናሳውቃለን ፡፡ የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤ/ቢሮ እና አጋሮቹ