Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የኩፍኝ ዘመቻ

ከግንቦት 0615/2017 ዓ.ም በክልል አቀፍ ለሚሰጠው የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ መሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደአለባቸዉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ ገለፁ ። (29/8/2017 ዓ.ም) የቢሮ ሀላፊው ዘመቻውን አስመልክቶ በክልሉ ለሚገኙ ሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በመግለጫቸው እንደአሉት ከግንቦት 06-15/2017 ዓ.ም በክልል አቀፍ ለሚሰጠው የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ መሳካት የሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደአለባቸዉ ነው ። የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑቁጥራቸዉ ከ204,465 በላይ ህፃናት በጤና ተቋማትና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የቢሮ ሀላፊው ገልጸዋል ። በዘመቻው ከተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ጋር እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች ለሆኑ ህፃናት በመደበኛ የክትባት መረሃ ግብር ያልተከተቡና ክትባት ጀምረዉ ያቋረጡ ህፃናትም ክትባት ይወስዳሉ ብዋል ። ከዚህም በተጨማሪ ከአምስት አመት በታች የሆኑና የታመሙ ህጻናት ልየታና ለህክምና መላክ፣የአጣዳፊ ምግብ እጥረት ልየታ የቫይታሚን ኤ ጠብታ መስጠት፣ የአንጀት ጥገኛ ትላትል ክኒን መስጠት ፣ ከወሊድ ጋር የተያያዘ የፊስቱላ ልየታና ምርመራ የማድረግ እና የCOVID-19 ክትባት መስጠት እንደሚሰጥ አቶ ወልተጂ ገልፀዋል፡፡ አቶ ወልተጂ አክለዉም ይህን ክትባት ዘመቻ ዉጤታማ ማድረግ የሚቻለው በጤና መዋቅሮች ብቻ ባለመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በተገኘው አጋጣሚ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማዳበር ለዘመቻው ስኬታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀው ከክልል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ያሉ የጤና ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የዘመቻውን ሂደት በየዕለቱ መገምገም እንደአለባቸዉ አሳስበዋል ።