Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ጤና መድህን

በመተከል ዞን ህብረተሰቡን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። (ሚያዝያ 24/2017 ዓ/ም) የክልሉ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከዞን አመራሮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በግልገል በለስ ከተማ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ እንዳሉት ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ የአዳዳስ አባላት የማፍራትና የነባር አባላት የዕድሳት ሥራዎች ከተጀመረ ወራትን እያስቆጠረ ቢሆንም በተፈለገው መልኩ ሥራው እየተሰራ አይደለም ብለዋል። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ በቀሪ ጊዜያት ዉስጥ ሥራዉን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እና በአሠራር ወቅት የነበሩ ክፍተቶችን ለይቶ አቅጣጫ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ የዉይይት መድረክ መዘጋጀቱን አቶ አለም ገልጸዋል ። ምክትል የቢሮ ኃላፊው አክለውም በአንድ አንድ ወረዳዎች ላይ የግንዛቤ ክፍተቶች መኖራቸውን ገልፀው ለዚህም በየደረጃ ያሉ አመራሩ እና ባለድርሻ አካላት በጋራ አበክረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ። የአባላት ምዝገባ በአንድ አንድ ወረዳዎች ከታቀደው በታች በመሆኑ ወደታች በመውረድ ግንዛቤ በመፍጠር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበት መሰራት እንዳለበት አቶ አለም ደበሎ ተናግረዋል ። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በበኩላቸው የጤና መድህን አገልግሎት በክልሉ ተግባራዊ በማድረግ ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረው አዳዲስ አባላት የማፍራት እና የነባር አባላት የዕድሳት ሥራዎች በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በትኩረት መስራት እንደአለባቸዉ አሳስበው ለተግባራዊነቱ የዞኑ መስተዳድር አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርግ ገልጸዋል ። የክልሉ ጤና ቢሮ በሁሉም አከባቢዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ስርዓቱን ለማጠናከር በሁሉም ወረዳዎች እገዛ የሚያደረግ የክትትልና ድጋፍ ቡድን የተመደበ ስለሆነ ለዞንና የወረዳ አመራሮች ከቡድኑ ጋር በመሆን አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈፀም አሳስበዋል ።