Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የኮሌራ ወረርሽን ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ አካላት እገዛ ወሳኝ ነው ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ስር ባሉ አከባቢዎች የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ለመግታት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባ ተገለፀ። (ሚያዝያ 24/2017 ዓ/ም) ከቢሮ የተወጣጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን በመተከል ዞን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል የክልል እና የዞን አመራሮች በተገኘበት በግልገል በለስ ከተማ ወይይት ተካሂዷል። ቡድኑ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ወረርሽኙን ለመከላከል እስከአሁን የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ጠንካራ አሰራሮች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ እና መሻሻል ያለባቸው አሰራሮች በአፋጣኝ እልባት ማግኘት እንደአለባቸዉ ተገልጿል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ እንዳሉት በዞኑ ስር ካሉ በአንድ አንድ ወረዳዎች የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል የሁሉም ወረዳ አመራሮች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የኮሌራ ወረርሽኝ በንፅህና ጉድለት የሚከሰት በመሆኑ ቸላ ሊባል የማይገባና ልዩ ቱክረት ተሰጥቶ ካልተሰራ ወረርሽኑ ወደ ሌሎች አከባቢዎች በመስፋፋት ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በበኩላቸው የኮሌራ ወረርሽኝ ወደ ሌሎች ወረዳዎች እንዳይዛመት ቀድሞ ለመከላከል አመራሩ እና ባለሙያዎች ወደታች በመውረድ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ዋና አስተዳዳሪው የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች ለጤና መዋቅሮች ብቻ የሚተዉ ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት አለባቸው ብለዋል። የኮሌራ ወረርሽኝን በተመለከተ አጠቃላይ ገለፃ ያደረጉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ምላሽ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መብራቱ በጉኖ በበኩላቸው የኮሌራ ወረርሽኝ በተበከለ ውሃና ምግብ አማካኝነት የሚከሰትና አጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ በማስከተል ለህልፈት የሚዳርግ አስከፊ በሽታ መሆኑን በማስረዳት ወረርሽኙን ለመከላከል የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ የመከላከል ሥራ ዉጤታማ ሊሆን የሚችለው አመራሩ በቁርጠኝነት ሥራዉን በየጊዜው እየገመገመ አቅጣጫ እየሰጠ በመሆኑ የመከላከል ሥራውን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት ወደ ሥራ ማስገባት እንደአለበት አቶ መብራቱ ተናግሯል ። በወይይት መድረኩ የተሳተፊት በበኩላቸው አመራሩ፣የጤና ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሽታውን ለመከላከልና ለመግታት የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው በውይይት መድረኩ ተገልጿል። በዉይይት መድረኩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ፣ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።