Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና ኤክሰቴንሽን ፍኖተ ካርታ

የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮገራም ሥራዎችን ዉጤታማ ለማድረግ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ ። (21/8/2017ዓ.ም) በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና ከዳንጉርና ከፖዌ ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ። በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀዉን የጤና ኤክሰቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ-ካርታ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ፕሮግራሙን የማስተዋወቅና በተመረጡ ወረዳዎች ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ። ይህንን በፖይለት ደረጃ በተወሰኑ ወረዳዎች የተጀመረዉን ፕሮግራም ወደ ሌሎች ወረዳዎች ለማስፋት በቀጣይ ፕሮግራሙ ሊተገበርባቸዉ ከታቀዱ ወረዳዎች ከጤና ጽ/ቤት፣ከጤና ጣቢያና ከጤና ኬላ ለተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠናው እንደሚሰጥ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ቡድን መሪ አቶ ግሩም ባዩ ገልጸዋል ። ስልጠናው የሚሰጠው በእናቶችና ህፃናት ጤና፣በበሽታ መከላከል፣በሀይጅንና ሳንቴሽንና በመረጃ ሥርዓት ላይ እንደሚሰጥ የገለፁት አቶ ግሩም የስልጠናው ዋና ዓላማ በጤና ጣቢያዎች ብቻ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ ጤና ኬላ ለማዉረድ የታሰበ መሆኑን ገልጸዋል ።