Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ፅዱና ንፀህ ኢትዮጵያ

በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እና ከመሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር የተያዘዉን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የፖዌ ወረዳ አመራሮች ገለፁ። (ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም) ፅዱና ንፁህ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ፕሮግራም በፖዌ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል ። በሀገር አቀፎ ደረጃ የተጀመረውን ፅዱና ንፁህ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ፕሮግራም ለማስተግበር እንደሀገር ከተመረጡ 52 ወረዳዎች መካከል የፖዌ ወረዳ አንዱ ነው ። ይህ ፕሮግራም የክልል ጤና ቢሮ፣የመተከል ዞን ጤና መመሪያ የሚመለከታቸው ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች፣የፖዌ ወረዳ አመራሮችና በፖዌ ወረዳ ስር የሚገኙ የቀበሌዎች ዋና አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ። በሀገራችን በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እና ከመሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር እንደሀገር ከተመረጡ ወረዳዎች 102 መካከል የፖዌ ወረዳ አንዱ ነው ። ይህንን ፕሮግራም በወረዳው ተግባራዊ በማድረግ ሀገራዊ ራዕይን እዉን ለማድረግ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃዉ ያሉ የአመራር አካላት እገዛ ወሳኝ በመሆኑ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ወረዳው ያሉ የአመራር አካላት በፅንሰ ሀሳቡ ላይ ግንዛቤ መፍጠር አሰፈላጊ በመሆኑ ለአመራር አካላት የግንዛቤና የንቅናቄ መድረክ ተዘጋጅቷል ። የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ የትዉዉቅ መድረኩን ሲከፊቱ እንደአሉት በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳትና ከመሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር የተያዘዉን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ነው ። በተለይም የደረጃዉ ያሉ የአመራር አካላት ሥራዉን በበላይነት በመምራትና ግንባር ቀደም ሞደል መሆን አለባቸው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪዉ አቶ አትንኩት ሽቱ ። ፅዱና ንፁህ አከባቢ መፍጠር ሜዳ ላይ መፀዳዳትንና መሽናት ለማስቀረት ፣የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት ሽፋን በማሻሻል ፣በጤና ተቋማት መሠረታዊ ሳንቴሽን በማስፋት፣ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል፣የአከባቢ ብክለትንና ማህበራዊ ቀዉስ በመቀነስና ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅም ለማሻሻል የጎላ ድርሻ ስለአለው ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪዉ ገልጸዋል ። የመተከል ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶ/ር ታሬቀኝ አርገታ በበኩላቸዉ ፅዱና ንፁህ አከባቢን በመፍጠር ዜጎች በልፅገዉ በክብር የሚኖሩባት ኢትዮጵያዊያን የማየት ዓላማ እዉን የሚያደርግ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባው ግልፀዋል ። የፖዌ ወረዳ ዋና አስተዳዳ አቶ ይርጋ አሠፋ ይህንን ፕሮግራም እዉን ማድረግ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን በመቀነስ፣ምርትና ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ጤናማ አምራችና ምቹ የሆነ ቦታ የሚኖር ማህበረሰብ ለመፍጠር የጎላ ድርሻ ስለአለው ለተግባራዊነቱ የወረዳው መንግስት አስፈላጊዉን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዉ ለተግባራዊነቱ በየደረጃዉ የሚገኙ የአመራር አካላት በቅንጅት መስራት እንደአለባቸዉ አሰገንዝበዋል ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የመሠረታዊ ጤናና የጤና ኤክሰቴንሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክብሩ ሰባኒ ወረዳዉ ፅዱና ንፁህ ኢትዮጵያ / አከባቢን በመፍጠር ዜጎቿ በክብር የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለማየት ወረዳው ለሚያደርገው እንቅስቃሴ በቢሮ በኩል አስፈላጊው ሁሉ እገዛ ይደረጋል ብለዋል። የፖዌ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው ፅዱና ንፁህ ኢትዮጵያን መፍጠር ከሚሰጠው የመንፈስ እርካታ በዘለለ ለጤና የጎላ ፋይዳ ስለአለው በትኩረት እንተገብራለን ብለዋል። በመጨረሻም የፖዌ ወረዳ መስተደድር ከሚመለከታቸዉ የፕሮግራሙ ፈፃሚ መ/ቤቶች መ/ቤቶች ጋር የትግበራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ።