Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የሆስፒታሎች የሥራ አፈጻጸም ግምገማ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የሚገኙ ሆስፒታሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሆስፒታሉ አመራሮች በትኩረት መስራት እንደአለባቸዉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ ገለፁ ። (18/9/2017 ዓ.ም) በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች የባለፉት የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄዷል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ የሥራ ግምገማ መድረኩን ሲከፊቱ እንደአሉትበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የሚገኙ ሆስፒታሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሆስፒታሉ አመራሮች በትኩረት መስራት እንደአለባቸዉ ነው። ሆስፒታሎች ከፍተኛ የሆነ የመልካም አሰተዳደር ጥያቄ የሚነሳባቸው ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን የሆስፒታል አመራሮች ከሆስፒታል ቦርድ ጋር በቅንጅት በመስራት የሆስፒታሎችን አገልግሎት በሚያሻሽሉ እና የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ በሚችሉ ጉዳዮች ለይተዉ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ቢሮ ሀላፊው ገልጸዋል ። ቢሮ ሀላፊው አክለውም የሆስፒታል አመራሮች መንግስት ለሆስፒታሎች ከሚመድበዉ በጀት ባለፈ የራሳቸውን በራሳቸው በማመንጨት የዉስጥ ገቢ አጠቃቀም በማሻሻል በሆስፒታሉ አስፈላጊ ግብዓቶችና አስፈላጊዉ የሰዉ ሀይል በማሟሟላት የተሻለ አገልግሎት በተቋሙ እንዲሰጥ ማድረግ አለባቸው ብለዋል። በተለይም የመድኃኒት ቁጥጥርና አሰተዳደር እና የአንቡላንስ አያያዝና አጠቃቀም ሥራዎች በልዩ ሁኔታ መመራት እንዳለባቸው የቢሮ ሀላፊዉ አሳስበዋል። በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች በተቀመጠላቸው እስታንደርድ መሠረት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ቢሮ በሁለተናዊ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ቢሮ ሀላፊው ገልጸዋል ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በበኩላቸው የሆስታሎችን አገልግሎት ለማሻሻል ሆስፒታሎች የዉስጥ ገቢ አሰባሰባቸዉና አጠቃቀም ዙሪያ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል። የሆስታሎች የግብዓት አቀርቦትን በማሻሻል በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችገሮች የመቅረፉ ጉዳዩ ልዩ ግምት ሊሰጠዉ እንደሚገባ አቶ አብዱልሙኒየም ተናግሯል ። የቦርድ አባላት የሥራ እንቅስቃሴ የማጠናከር እና የመረጃ ሥርዓት የማጠናከር የበለጠ በትኩረት መሰራት እንደአለባቸዉ ምክትል የቢሮ ሀላፊው አስገንዝቧል ። በመድረኩ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ጥምረት ለጥራት በመጀመሪያ ዙር ለተገበሩ ወረዳዎችና ጤና ጣቢያዎች የእዉቅና አሰጣጥና የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የሁለተኛ ዙር ትግበራ ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል ።