Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የካማሽ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ ነው

የካማሽ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተገለፀ። (6/8/2017ዓ.ም) የካማሽ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስከያጅ ሲስተር አበባዬ አቦማ እንደአሉት የሆስፒታሉን የአገልግሎት በማሻሻል ጥራት ያለውን አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ። ሆስፒታሉ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የሰዉ ሀይል እና የህክምና ግብዓቶች በማሟላት አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሲስተር አበባዬ ገልጸዋል ። በሆስፒታሉ በተመላላሽና በተኝቶ ህክምና በርካታ ታካሚዎችን እንደሚያስተናግድ የገለፁት ሥራ አስከያጇ የእናቶች ህፃናት ሞት የመቀነስ ሥራዎች በልዩ ሁኔታ ይሰራሉ ብለዋል። ሆስፒታሉ በመደበኛነት ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ በአከባቢው ለሚገኙ የጤና ጣቢያዎች የእዉቀት ሽግግር እና አልፎ አልፎ በዞኑ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች ላይ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ መሆኑን ሲስተር አበባዬ ገልፀው ለሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ማኔቆ የሆኑ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች በሚመለከታቸው አካላት ሊታሰብበት እንደሚገባ ጠይቀዋል ።