Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ንቅናቄ

የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም በማጠናከር በዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ዘንድ በትኩረት እንደሚሰራ ለመስራት የቤልዲጊሉ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሀመድ አብዱዛየር አስታውቀዋል፡፡ በቤልዲጊሉ ወረዳ የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም አስመልክቶ የማህበረሰብ ተሳትፎና ባለቤትነት ለማጠናከር ለጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎችና በተዋረድ ለሚገኙ አመራሮች የግንዛቤና የንቅናቄ መድረክ በቤልዲጊሉ ከተማ ተካሂደዋል፡፡ በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በክሪ አብዲላሂ በጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም ዙሪያ የማህበረሰብ ተሳትፎና ባለቤትነት ለማጠናከር የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የግንዛቤ መስጫ ሰነዱን ያቀረቡት የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴሽንና መሰረታዊ ጤና አገልግሎት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክብሩ ሰባኒ በበኩላቸው አዲሱ የማህበረሰብ ማሳተፊያ አደረጃጀት በጤና ኤክሰቴሽንና ሌሎች አደረጃጀቶች መካከል ወንዶች፣ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ተቋማት ትስስር ለመፍጠርና ኮሚኒኬሽን ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል። በተሰጠው የግንዛቤ መድረክ ላይ የብልዲጊሉ ወራዳ የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤት ሀላፊዎች፣ የአሶሳ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ፣ከክልሉ ጤና ቢሮ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና በቤልዲጊሉ ወረዳ ስር የሚገኙ ሁሉም ቀበሌ አመራሮችና የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች ተገኙተዋል፡፡