Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም

የጤና ኤክሰቴንሽን ፕሮግራም ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ ። (3/8/2017 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን እና መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክብሩ ሰባኒ በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ተቀዛቅዞ የነበረውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ወደ ነበረበት በመመለስ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ፕሮግራሙን መልሶ ለማጠናከር ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በጤና ኤክሰቴሽን ፕሮግራም ዙሪያ የንቅናቄ ሥራዎች መሰራታቸውን አቶ ክብሩ ገልጸዋል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን ያጠናክራል ተብሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን የጤና ኤክሰቴንሽን ፍኖተ ካርታ የማስተዋወቅና የማስተግበር ሂደቶች መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ተናግሯል ። በተካሄዱ የንቅናቄ መድረኮች የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ወደ ሥራ ስለመግባቱ ለማረጋገጥ በተደረገው ድጋፋዊ ጉብኝት አብዛኛው ቀበሌዎች ወደ ሥራ መመለሳቸውን የገለፁት አቶ ክብሩ ሙሉ በሙሉ ፕሮግራሙን ወደ ሥራ ለማስገባት የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠይቀዋል ። አቶ ክብሩ አክለውም በቢሮ በኩል በተለያዩ ምክንያት አገልግሎት ያቋረጡ የጤና ተቋማትን ወደ ሥራ የማስገባት፣ግብዓቶችን የማሟሟላትና የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በመሰጠት ላይ ናቸው ብለዋል። የጤና ኤክሰቴንሽን ፕሮግራም ሥራዎች ዉጤታማ የሚሆነው በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ብቻ ባለመሆኑ መላው ማህቀረሰብ በጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጅ የተቀመጡ ተግባራትን በመተግበር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደአለባቸዉ ጥሪ አቀርበዋል ።