Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት መሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር በጋራ እንስራ!!

በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እና ከመሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር የተያዘዉን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ ። ቢሮው በፅዱና ንፁህ አከባቢ የመፍጠር ገራዊ ራዕይ ላይ ያተኮረ ዉይይት ከአቡራሃሞ ወረዳ በየደረጃው ከሚገኙ የአመራር አከካላት ጋር መክሯል ። በሀገራችን በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እና ከመሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር እንደሀገር ከተመረጡ ወረዳዎች 50 መካከል የአቡራሃሞ ወረዳ አንዱ ነው ። ይህንን ፕሮግራም በወረዳው ተግባራዊ በማድረግ ሀገራዊ ራዕይን እዉን ለማድረግ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃዉ ያሉ የአመራር አካላት እገዛ ወሳኝ በመሆኑ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ወረዳው ያሉ የአመራር አካላት በፅንሰ ሀሳቡ ላይ ግንዛቤ መፍጠር አሰፈላጊ በመሆኑ ለአመራር አካላት የግንዛቤ እና የንቅናቄ መድረክ ተዘጋጅቷል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር የንቅናቄ መድረኩን ሲከፊቱ እንደአሉት በ2030 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እና ከመሽናት ነፃ የሆነ አከባቢ ለመፍጠር የተያዘዉን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ነው በተለይም ቀየደረጃዉ ያሉ የአመራር አካላት ሥራዉን በበላይነት በመምራት እና ግንባር ቀደም ሞደል መሆን አለባቸው ብለዋል ምክትል ሀላፊው ። ፅዱና ንፁህ አከባቢ መፍጠር ሜዳ ላይ መፀዳዳትንና መሽናት ለማስቀረት ፣የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት ሽፋን በማሻሻል ፣በጤና ተቋማት መሠረታዊ ሳንቴሽን በማስፋት፣ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል፣የአከባቢ ብክለትንና ማህበራዊ ቀዉስ በመቀነስና ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅም ለማሻሻል የጎላ ድርሻ ስለአለው ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ አቶ አብዱልሙኒየም ገልጸዋል ። ምክትል ሀላፊዉ አክለዉም ፅዱና ንፁህ አከባቢን በመፍጠር ዜጎች በልፅገዉ በክብር የሚኖሩባት ኢትዮጵያዊያን የማየት ዓላማ እዉን የሚያደርግ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባው አሳስበዋል ። የአቡራሃሞ ወረዳ አቶ ባብክር ሀሚዲ በበኩላቸው ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን በመቀነስ፣ምርትና ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ እና ጤናማ ፣ አምራች ፣እና ምቹ የሆነ ቦታ የሚኖር ማህበረሰብ ለመፍጠር የጎላ ድርሻ ስለአለው ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጸዋል ። በመጨረሻም የክልሉ ጤና ቢሮ ከአቡራሃሞ ወረዳ ከተወጣጡ ሴክተር መ/ቤቶች ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ።