Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

Asossa general hospital

በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደጋጋሚ በሀኪሞች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መታረም እንደአለበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ አሳሰቡ ።የጤና ቢሮ ሀላፊዎች ከሆስፒታሉ ሀኪሞችና የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያይቷል ። (30/7/2017 ዓ.ም) እኛ የአሶሳ አጠቃላይ ሀኪሞች በተመደብንበት የሙያ መስክ ላይ በቅንነት እና በታታሪነት ዜጎችን በማገልገል ላይ እያለን በተለያዩ ጊዜያት በህክምና ባለሙያዎች ላይ በተለያዩ ምክንያቶች በሥራ ላይ እያለን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየደረሰብን ስለሆነ ሰብዓዊ መብታችን ይከበርልን በማለት የተቋሙ ሀኪሞች በዉይይት መድረኩ ላይ አንስተዋል ። እኛ በተመደብንበት የሙያ መስክ ላይ በቅንነት እና በታታሪነት ዜጎችን ለማገልገል ዝግጁ በመሆናችን በሆስፒታሉ በኩል ለሥራችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎች እንደመቻቹላቸዉ ጠይቀው ችግሮች ሲፈጠሩ ከመባባሱ በፊት በወቅቱ መፍትሄ እያገኙ መሄድ አለባቸው ብለዋል። የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የሀኪሞችም ሆነ የህሙማን ደህንነት ለማስጠበቅ አሁን ያለዉ የግቢ ጥበቃ እና የአስተማሚዎች ፍሰት ሥራዎች አመችና አስተማማኝ ባለመሆኑ በቀጣይ መስተካከል እንደአለበት ባለሙያዎች ጠይቀዋል ። የጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በአሶሳ አጠቀላይ ሆስፒታል የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እና ምቹ የሥራ ሁኔታዎች ለመፍጠር ቢሮው በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ የሆስፒታሉን የግቢ ደህንነት የማስጠበቅ እና በሆስፒታሉ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላት ተግባር በመሆኑ የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አካላት ሀላፊነት በመሆኑ ማኔጅመንቱ ወደ ሥራ መግባት አለበት ብለዋል። የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስከያጅ አቶ ጃፈር መርቅኔ በበኩላቸው በሆስፒታሉ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የስነ ምግባር ጉድለቶች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በድጋሚ እንዳይሰቱ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት በትኩረት እንደሚሰራ ገለፀዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገዉ የዉይይት መድረክ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደጋጋሚ በሀኪሞች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መታረም አለበት ብለዋል። በተለይም እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት ክትትል ማድረግ እንደአለበት የገለፁት የቢሮ ሀላፊው ከሆስፒታሉ ማኔጅመንት አቅም በላይ ከሆነ በቢሮው በኩሉ አስፈላጊው እገዛ ያደርጋል ብለዋል። የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አካላት በሆስፒታሉ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችገሮችንና የግብዓት እጥረቶችን ለመቅረፍ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት በየጊዜው ሥራዎችን እየገመገሙ በሆስፒታሉን የሚስተዋሉ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ መምራት እንደአለበት የቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል